መልዕክት ለወጣቶች
ማንነትን መጠበቅ
ማንም ሰው በሌሎች አእምሮ የሚመራ ማሽን ለመሆን መስማማት የለበትም፡፡ እግዚአብሔር የማሰብና የማድረግ ችሎታ ሰጥቶናል፡፡ በጥንቃቄ በመተግበርና ለጥበብ ወደ እርሱ በመመልከት የህይወትን ሸክሞች ለመሸከም ትችላላችሁ፡፡ እግዚአብሔር የሰጠህን ማንነት ይዘህ ቁም፡፡ የሌላ ሰው ጥላ አትሁን፡፡ ጌታ በአንተ ውስጥና በአንተ አማካይነት እንደሚሠራ እወቅ፡፡ MYPAmh 126.4
በቂ ትምህርት ስላለህ ብዙ ጥረት እንደማያስፈልግህ አይሰማህ፡፡ የሰው መለኪያው የተማረ አእምሮ ነው፡፡ ትምህርት በዕድሜ ልክ ሁሉ መቀጠል አለበት፡፡ በቀኑ እየተማርክ ያገኘኸውን እውቀት ተግባራዊ ጥቅም ላይ ማዋል አለብህ፡፡ MYPAmh 126.5
የምታገለግሉት በማንኛውም ደረጃ ቢሆን ውስጣዊ ማንነታችሁን እየገለጣችሁና ባሕርይን እያሳደጋችሁ ነው፡፡ የምታደርጉትን ሁሉ በትክክለኛነትና በትጋት ሥሩ፡፡ ቀላል ሥራ የመፈለግ ዝንባሌን ተቋቋሙ፡፡ MYPAmh 126.6