መልዕክት ለወጣቶች

196/511

መሰራታዊ የሆኑ ነገሮችን በጥልቀት ማስተዋል

ዝቅተኛ በሆነ ደረጃ በፍፁም ረክታችሁ አትረፉ፡፡ ትምህርት ስትማሩ በሌሎች እይታ የከበራችሁና ቅዱስ ሆናችሁ ለመገኘታችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ በእግዚአብሔር የወይን ቦታ በአንዱ ክፍል ራሳችሁን ለአገልግሎት ገጣሚ ለማድረግ ስለምትሹ ሂዱ፡፡ ከዚህ ግብ ለመድረስ ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አደርጉ፡፡ ማንም ሰው ለእናንተ ማድረግ የማይችለውን ነገር ለራሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ለራሳችሁ ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ብታደርጉ ምንኛ ከባድ ሸክም ከርዕሰ-መምህራችሁና ከመምህራኖቻችሁ ታነሱ ነበር! MYPAmh 120.6

ከፍ ያሉ የሥነ-ጽሁፍ ዘርፎችን ለመማር ጥረት ከማድረጋችሁ በፊት ቀለል ያሉ የእንግሊዝኛ ሰዋሰው ህጎች አጠቃላይ እውቀት እንዳላችሁና ማንበብ፣ መፃፍና ፊደላትን በትክክል መጥራት መቻላችሁን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ MYPAmh 120.7

በወደፊት ሕወታችሁ ጠቀሜታው አነስተኛ የሆነ ነገርን በመማር ጊዜያችሁን አታባክኑ፡፡ የጥንት ሥነ-ፅሁፎችን እውቀት ለማግኘት ከመጣር ይልቅ በመጀመሪያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትክክል መናገርን ተማሩ፡፡ የሂሳብ አያያዝንም ተማሩ፡፡ ባለህበት ሁሉ ጠቃሚነትህን በሚጨምሩ የትምህርት ዘርፎች እውቀትን አካብት፡፡ Counsels to Teachers, Parents and Students, p. 218-219. MYPAmh 120.8