መልዕክት ለወጣቶች
ባሕርይና ፀባይ
ከህይወት ውኃ እየጠጡ ያሉ እንደ ዓለማውያን ለለውጥና ደስታን ለማግኘት አይቋምጡም፡፡ በባሕርያቸውና በአካሄዳቸው በየዕለቱ ግራ የሚያጋባቸውን ነገርና ሸክማቸውን በኢየሱስ ላይ በመጣል ያገኙት እረፍት፣ ሰላምታና ደስታ ይታይባቸዋል፡፡ በታዛዥነት መንገድና ተግባርን በታማኝነት በመፈጸም እርካታና ደስታ መኖሩን ያሳያሉ፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ሁሉ ሊታይ የሚችል ተጽእኖ በጓደኞቻቸው ላይ ያሳድራሉ፡፡ MYPAmh 119.2
ትጉህ፣ አስተዋይና ታማኝ የሆነ አንድ በትምህርት ቤት ውስጥ ያለ ወጣት ዋጋው ከግምት ያለፈ እንቁ ነው፡፡ የሰማይ መላእክት በፍቅር እይታ ይመለከቱታል፡፡ እያንዳንዱ የጽድቅ ሥራ፣ እያንዳንዱ የተቋቋመው ፈተና፣ እያንዳንዱ ያሸነፈው ክፋት በሰማይ መዝገብ ተመዝግቧል፡፡ የዘላለም ሕይወትን ማግኘትና ሊመጣ ያለውን ጊዜ ማለፍ የሚያስችል ጥሩ መሰረት ላይ እየታነፀ ነው፡፡ MYPAmh 119.3
እግዚአብሔር ሥራው ወደ ፊት እንዲቀጥል ያቀዳቸውን ተቋማት የማቆየትና የመጠበቅ ኃላፊነት በአብዛኛው በክርስቲያን ወጣቶች ላይ ያርፋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ውጤታቸው በጣም አስፈላጊ የሆኑ ኃላፊነቶች በሰው ልጅ የትውልድ ዘመን ያረፉበት ሌላ ወቅት አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ታላቅ ሥራ እንዲጠቀምባቸው ወጣቶች ራሳቸውን ማዘጋጀት ምንኛ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሌሎች ሁሉ አስፈላጊ የሆነ ነገር እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ይፈልግባቸዋል፡፡ MYPAmh 119.4