መልዕክት ለወጣቶች

190/511

በሚስዮን የሥራ መስክ

በተግባራዊ ሕይወት በሁሉም አቅጣጫዎች መሰልጠን ወጣቶቻችን ትምህርት ቤትን ለቀው ወደ ውጭ ሀገሮች ሲሄዱ ጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ምግብ ለማዘጋጀት ወይም ልብስ እንዲሰፉላቸው ወይም ቤት እንዲሠሩላቸው በሌሎች ጥገኛ አይሆኑም፡፡ ሌሎችን ያልተማሩትን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰሩ ሊያስተምሯቸው እንደሚችሉና የተሻለ ውጤ እንዲያመጡ እንደሚያደርጉአቸው ቢያሳዩ የበለጠ ተቀባነት ይኖራቸዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሚስዮናውያን በትምህርታቸው ላይ የአካል ኃይላቸውን ጠቃሚ ከሆነ ተግባራዊ የጉልበት ሥራ ጋር ስላዋሀዱ ለኑሮአቸው ጥቂት ገቢ ካለ ይበቃቸዋል፡፡ ገንዘብ ለማግኘት አሰቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የዚህ ዓይነት ሰዎች በጣም ተፈላጊ ናቸው፡፡ ሚስዮናውያን እንዴት የጉልበት ሥራ ሠርቶ መኖር እንደሚቻል ማስተማር እንደሚችሉ ያሳያሉ፡፡ በሄዱበት ሁሉ በዚህ መስመር ያገኙት ነገር ሁሉ የመቆሚያ ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡ Counsels to Teachers, Perents & Students, P.307-314. MYPAmh 118.6