መልዕክት ለወጣቶች

188/511

ጠቃሚ ከሆነ የጉልበት ሥራ የሚገኝ ጥቅም

በጨዋታ መልክ ከሚደረግ ወይም ተራ ከሆነ የአካል እንቅስቃሴ ታላቅ ጥቅም አይገኝም፡፡ ንፁህ አየር ባለበት በመሆን ወይንም ከጡንቻዎች እንቅስቃሴ ጥቂት ጥቅም ይገኛል፡፡ ነገር ግን ለዚህ አይነት እንቅስቃሴ የሚወጣውን ያህል ጉልበት ጠቃሚ ለሆነ ሥራ ብናውል ጥቅሙ ትልቅ ይሆናል፡፡ የዚህ አይነት እንቅስቃሴ በውስጡ ጠቃሚ ሰው የመሆንን ስሜት ስለሚፈጥር በተገቢ ሁኔታ ለተሰራው ሥራ የህሊና ማረጋገጫ ይሰጥና የእርካታ ስሜት ይፈጥራል፡፡ MYPAmh 117.5

ተማሪዎች ከትምህርት ቤቶቻችን ሲወጡ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን በትምህርት የተደገፈ ብቃት ይዘው መውጣት አለባቸው፡፡ ይህ ሲሆን፣ ያሏቸውን ክህሎቶች እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ ሁኔታ ሲፈጠር በህይወት ስኬትን ለማግኘት አስፈላጊ የሆነ ሊጠቀሙበት የሚችሉት እውቀት ይኖራቸዋል፡፡ ተግቶ መማር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ተግቶ መስራትም አስፈላጊ ነው፡፡ የአካል ኃይሎችን ለመደሰቻ ማዋል ሚዛናዊ ለሆነ አእምሮ አይመችም፡፡ MYPAmh 118.1

ለአካል እንቅስቃሴ የሚውልና ደረጃ በደረጃ ከሚፈለገው መጠን ወደ ማለፍ የሚሄደው ጊዜ ክርስቶስ በሚፈልገው መንገድ ለመስራት ጥቅም ላይ ቢውል ኖር በሠራተኛው ላይ የእግዚአብሔር በረከት ያርፍ ነበር፡፡ የጉልበት ሥራን ከአእምሮ ሥራ ጋር በማዋሃድ የሚገኝ ለተግባራዊ ሕይወት የሚረዳ ራስን መግራት ጣፋጭ የሚሆነው እግዚአብሔር ሰዎች እንዲሰሩት ለሚፈልገው ሥራ በተሻለ ሁኔታ ብቁ እንዲሆኑ አያደረጋቸው ስለሆነ ነው፡፡ ወጣቶች የህይወትን ተግባራት እንዴት በትክክል እንደሚሠሩ ሲያስተውሉ ለሌሎች ከሚኖራቸው ጠቀሜታ አንፃር ከዕለት ወደ ዕለት የሚኖራቸው ደስታ ታላቅ ይሆናል፡፡ ጠቃሚ የጉልበት ሥራ መስራትን የተማረ አእምሮ ይሰፋል፡፡ በሥልጠናና በመግራት ለጠቃሚነት ገጣሚ ይሆናል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ለባለቤቱ በረከት የሚሆን ጠቃሚ እውቀት ስላገኘ ነው፡፡ MYPAmh 118.2

በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ ጊዜውን ለጨዋታና ለመዝናናት የሰዋውን አጋጣሚ ማግኘት አልችልም፡፡ እርሱ ለአሁንም ሆነ ለወደፊቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ታላቅ መምህር ነበር፡፡ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ የአካል እንቅስቃሴን ለማድረግ የመዝናኛ ተግባር ላይ እንዲሠማሩ ያስተማረበት አንዲት አጋጣሚ እንኳ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ MYPAmh 118.3