መልዕክት ለወጣቶች
ክርስቶስ ብቸኛው ተስፋችን
ክርስቶስ ተሰቃይቷል፣ ተሰድቧል፣ ተደብድቧል፡፡ በግራም በቀኝም የፈተና ጥቃት ደርሶበታል፡፡ ሆኖም ኃጢአት አልሰራም፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አጥጋቢ የሆነ ፍፁም መታዘዝን ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ ይህንን በማድረግም ላለመታዘዝ እንደ ምክንያት የሚቀርበውን እያንዳንዱን ሰበብ አስወገደ፡፡ እርሱ ለሰው እንዴት መታዘዝ እንዳለበትና እንዴት ሁሉንም ትዕዛዛት መጠበቅ እንደሚቻል ለማሳየት መጣ፡፡ መለኮታዊ ኃይልን ጨበጠ፤ ይህ የኃጢአተኛ ብቸኛ ተስፋ ነው፡፡ ሰው በፍትወት ምክንያት በዓለም ውስጥ ካለው እርኩሰት አምልጦ የመለኮታዊው ባሕሪይ ተካፋይ ይሆን ዘንድ ራሱን ሰጠ፡፡ MYPAmh 109.1
እግዚአብሔር ለክብሩ ይጠቀሙአቸው ዘንድ ለወጣቶች መክሊቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች እነዚህን ስጦታዎች ላልተቀደሰ ተግባር ይጠቀማሉ፡፡ ብዙዎች ወጣቶች በትክክል ጥቅም ላይ ቢውሉ ኖሮ የበለፀገ የአእምሮ፣ የግብረገብና የአካል ብርታትን ሊያመጡ የሚችሉ ችሎታዎች አሉአቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ቆም ብለው አያስቡም፡፡ የተግባር አቅጣጫቸው የሚያስከፍላቸውን ዋጋ አይቆጥሩትም፡፡ ምክርንና ተግሳፅን የማይሰማ ግድየለሽነትንና ከንቱነትን ያደፋፍራሉ፡፡ ይህ አሳቃቂ ስህተት ነው፡፡ ወጣቶች የእግዚአብሔር ዓይን በእነርሱ ላይ መሆኑንና የእግዚአብሔር መላእክት የባህሪያቸውን እድገት እንዲሚመለከቱና የግብረገብ ብቃታቸውን እየመዘኑ መሆናቸውን ቢገነዘቡ ኖር አእምሮአቸው ትሁት ይሆን ነበር፡፡ The Youth’s Instructor, July 27,1899. MYPAmh 109.2