መልዕክት ለወጣቶች

162/511

የመንፈስ ቅዱስ የፀጥታ ሥራ

የክርስቲያን ሕይወት አሮጌውን ማሻሻል ወይንም ማደስ ሳይሆን የተፈጥሮ ለውጥ ነው። ለራስና ለኃጢአት በመሞት ሙሉ በሙሉ አዲስ ሕይወትን መልበስ ነው። ይህ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ ውጤታማ ሥራ ብቻ ነው። MYPAmh 104.1

ኒቆዲሞስ ግራ ተጋብቶ በነበረ ሰዓት ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ትርጉሙን ለመግለፅ ንፋስን ተጠቀመ። «ንፋስ ደስ ወዳለው ይነፍሳል። ድምፁንም ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣና ወዴትስ እንደሚሄድ አታውቁም። ከመንፈስ ቅዱስ የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው፡፡” MYPAmh 104.2

ንፋስ በዛፎችና በቅርንጫፎች መካከል ቅጠሎችንና አበቦችን በማንቀሳቀስ ይሰማል። ሆኖም ስለማይታይ ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ ማንም ሰው አያውቅም፡፡ በልብ ውስጥም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ እንደዚሁ ነው። ከንፋስ እንቅስቃሴ በተሻለ ሁኔታ ሊብራራ አይችልም:: አንድ ግለሰብ በሕይወቱ ለውጥ የመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ ወይም ቦታ ወይም በመለወጥ ሂደት ውስጥ የነበሩ ሁኔታዎችን በሙሉ መግለፅ አይችልም ይሆናል። ይህን ማድረግ አለመቻሉ ግን ላለመለወጡ ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። ልክ እንደ ንፋሱ በማይታይ ወኪል አማካኝነት ክርስቶስ ያለማቋረጥ በልብ ውስጥ ይሰራል። ትንሽ በትንሽ ምናልባትም ተቀባዩ ሳይገነዘበው ነፍስን ወደ ክርስቶስ የሚስቡ አሻራዎች ተፈጥረዋል። ይህንን መቀበል የሚቻለው ቃሉን በማንበብና በእርሱ ላይ በማሰላሰል ወይንም ከዚያው ሰባኪ ቃል በመስማት ሊሆን ይችላል። በድንገት መንፈስ ቀጥተኛ ተማፅኖውን ይዞ ሲመጣ ነፍስ በደስታ ራሱን ለኢየሱስ አሳልፎ ይሰጣል። በብዙዎች ይህ ቅጽበታዊ መለወጥ ይባላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በትዕግስት ለረጅም ጊዜ የመማፀን ውጤት ነው። MYPAmh 104.3

ንፋስ በራሱ የማይታይ ቢሆንም የሚታዩና የሚዳሰሱ ውጤቶችን ያመጣል:: እንደዚሁ በነፍስ ላይ የመንፈስ ሥራ የእርሱን የማዳን ኃይል በተሰማው ግለሰብ እያንዳንዱ ድርጊት ራሱን ይገልፃል። የእግዚአብሔር መንፈስ ልብን ሲቆጣጠር ሕይወትን ይለውጣል። የኃጢአት አስተሳሰቦች ይተዋሉ ! ክፉ ሥራዎችም እንደዚሁ። ፍቅር፣ ራስን ዝቅ ማድረግና ሰላም የቁጣን፣ የቅናትንና የጠብን ቦታ ይወስዳሉ። የሐዘንን ቦታ ደስታ ይወስድና ፊት የሰማይን ብርሃን ያበራል። ሸክምን የሚያነሳውን እጅም ሆነ ከላይኛው አደባባይ ብርሃን ሲወርድ ማንም አያይም። ነፍስ በእምነት ራሱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ ሲሰጥ በረከት ይመጣል….። MYPAmh 104.4

ለውስን አእምሮ የደህንነትን ሥራ ሙሉ በሙሉ ማስተዋል የማይቻል ነው። የደህንነት ምስጢር ከሰብዓዊ እውቀት በላይ ነው። ሆኖም ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ሰው መለኮታዊ እውነታ መሆኑን ይገነዘባል። የደህንነትን ጅምር እዚሁ በግል ልምምዳችን ልናውቀው እንችላለን። ውጤቶቹ ዘላለምን የሚዘልቁ ናቸው። Desire of Ages, P.172-173. MYPAmh 104.5