መልዕክት ለወጣቶች
ለተሰጠን ብርሃን ተጠያቂነት
ወጣት ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሐየር ለሰጠን ብርሃን ተጠያቂዎች ነን። ይህ ብርሃንና እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች በደንብ ካልተደመጡ በእኛ ላይ ፍርድ ያመጣሉ፡፡ አደጋው በግልጽ ተነግሮአችኋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ላይ እንዳትወድቁ ማስጠንቀቂያ ተቀምጦላችኋል፡ በማስጠንቀቂያዎች ታጥራችኋል። በእግዚአብሔር ቤት በመንፈስ ቅዱስ አመራር ከእግዚአብሔር ባሪያዎች አፍ እጅግ የከበሩና ልብን የሚመረምሩ እውነቶችን አድምጣችኋል። እነዚህ የከበሩ ተማፅኖዎች በልባችሁ ውስጥ ምን ያህል ክብደት ተሰጥቷቸዋል? በባህሪያችሁ ላይስ ምን ያህል ተፅዕኖ አሳድረዋል? ለእነዚህ ለእያንዳንዱ ተማፅኖዎችና ማስጠንቀቂያዎች ተጠያቂ ትሆናላችሁ። እነዚህ ቃላት የከንቱነትን፣ MYPAmh 97.1
የፌዛኝነትንና የኩራትን ሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ላይ በፍርድ ቀን ለኩነኔ ይነሱባቸዋል። ውድ ወጣት ወዳጆቼ! የዘራችሁትን ያንኑ ታጭዳላችሁ። ለእናንተ የመዝሪያ ሰዓቱ አሁን ነው። መከሩ ምን ይሆን ይሁን? ምን እየዘራችሁ ነው? እያንዳንዱ የምትናገሩት ቃል፣ እያንዳንዱ የምትሰሩት ሥራ መጥፎ ወይንም ጥሩ ፍሬ ሊያፈራ የሚችል ዘር ነው። በመጨረሻም ለዘሪው ደስታን ወይንም ሐዘንን ሊያመጣ ይችላል፡፡ መከሩ በዘር ሁኔታ ይወሰናል። እግዚአብሔር ታላቅ ብርሃንና ብዙ እድሎችን ሰጥቷችኋል። ብርሃኑ ከተሰጣችሁና አደጋዎቹ በግልፅ ከተቀመጡላችሁ በኋላ ሃላፊነቱ የእናንተ ይሆናል። እግዚአብሔር የሰጣችሁን ብርሃን የምትይዙበት ሁኔታ ሚዛኑ ወደ ደስታ ወይም ወደ ዋይታ እንዲያጋድል ያደርገዋል። የወደ ፊት መዳረሻችሁን ለራሳችሁ እየሰራችሁ ናችሁ። Testimonies for the Churches, Volume 3, P. 363. MYPAmh 97.2