መልዕክት ለወጣቶች

147/511

የተስተካከለ ባሕርይ

ለእግዚአብሔር ሥራ ያለንን ንብረት ለመስጠት ፈቃደኛ ልንሆን እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ለእርሱ የፍቅርና የአመስጋኝነት ልብ ካልሰጠነው በስተቀር ይህ ዋጋ አይኖረውም፡፡ በውጭ የሥራ መስክ እውነተኛ ሚስዮናውያን መሆን የሚፈልጉ በመጀመሪያ በአገር ውስጥ እውነተኛ ሚስዮናውያን መሆን አለባቸው፡፡ በጌታ የወይን ቦታ መስራት የሚፈልጉ ሰዎች እርሱ እንዲጠነቀቁለት የሰጠውን ትንሹን የወይን ቦታ በጥንቃቄ በመንከባከብ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው ፡፡ MYPAmh 95.6

«ሰው በልቡ እንደሚያስብ እንዲሁ ነው፡፡» ብዙ ሐሳቦች የእለቱን ያልተፃፈ ታሪክ ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ሐሳቦች ባህርይን በመመስረት ረገድ ብዙ ድርሻ አላቸው፡፡ አንድ ንጽህና የጎደለው ሐሳብ በነፍስ ላይ ጥልቅ አሻረ ስለሚያሳርፍ ሐሳቦቻችን በጥብቅ መጠበቅ አለባቸው፡፡ መጥፎ ሐሳብ በአእምሮ ውስጥ መጥፎ አሻራን ይተዋል፡፡ ሐሳቦቹ ንፁህና ቅዱስ ከሆነ ግለሰቡ እነዚህ ሐሳቦች ስላሉት የተሻለ ሰው ይሆናል፡፡ በእነርሱ አማካይነት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ይፋጠናል፤ መልካም የማድረግ ኃይልም ይጨምራል፡፡ አንድ የዝናብ ጠብታ መሬቱን በማረስረስ ለሌለኛው ጠብታ እንደሚያዘጋጅ ሁሉ አንድ መልካም ሐሳብም ለሌላ መልካም ሐሳብ መንገድ ያዘጋጃል፡፡ MYPAmh 95.7

ረዥም ጉዞ መጎዝ የሚቻለው አንድ ጊዜ አንድ እርምጃን በመራመድ ነው፡፡ ተከታታይ እርምጃዎች ወደ ጉዞው ፍፃሜ ያደርሱናል፡፡ ረዥም ሰንሰለት የተሰራው ከተናጠል የብረት ቀለበቶች ነው፡፡ ከነዚህ አንዱ ቀለበት ጉድለት ካለበት ሰንሰለቱ ዋጋ-ቢስ ነው፡፡ ባህሪይን በተመለከተም እንዲሁ ነው፡፡ MYPAmh 95.8

የተስተካከለ ባህሪይ የሚመሰረተው በትክክል በተከናወኑ የተናጥል ተግባራት ነው፡፡ በማሸነፍ ፋንታ ያዳባርነው አንድ ጉድለት ግለሰቡን ፍጽምና የጎደለው በማድርግ የቅድስና ከተማ ደጆችን ይዘገበታል፡፡ ወደ ሰማይ የሚገባ ሰው ነቁጣ፣ የፍት መጨማደድ ወይም ማንኛውም ይህንን የሚመስል ነገር የሌለበት ባህርይ ሊኖረው ይገባል፡፡ የሚያረክስ ከንቱነት ወደዚያ አይገባም፡፡ በዳኑት ሠራዊት መካከል አንድም ጉድለት አይታይባቸውም፡፡ MYPAmh 95.9