መልዕክት ለወጣቶች
ከሁሉ አነስተኛ በሆነው ታማኝ መሆን
“ከሁሉ ትንሽ በሆነው የታመነ በብዙም የታመነ ይሆናል።” MYPAmh 95.1
ሕይወትን ስኬታማ የሚያደርገው ዓለም ‹ትንሽ ነገሮች› ለሚላቸው ተገቢውን ትኩረት መስጠት ነው። ትንንሽ የበጎ አድራጎት ተግባሮች፣ ትናንሽ ራስን የመካድ ድርጊቶች፣ ጠቃሚ የሆኑ ቀላል ቃላትን መናገር፣ ከትናንሽ ኃጢአቶች መጠንቀቅ-ክርስትና ማለት ይህ ነው። ለየእለቱ በረከቶች አመስጋኝ መሆን፣ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ዕድሎች በጥበብ ማሻሻል፣ የተሰጡንን መክሊቶች በትጋት መንከባከብ- ጌታ እየጠራን ያለው ለዚህ ነው። MYPAmh 95.2
ትናንሽ ተግባራትን በታማኝነት የሚፈጽም ሰው የታላላቅ ኃላፊነቶችን ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ይሆናል። በዕለታዊ ሕይወቱ ደግና ትሁት የሆነ ሰው፣ በቤተሰቡ ውስጥ ለጋስና ታጋሽ የሆነ ሰው፣ የሁል ጊዜ ዓላማው ቤቱን ደስተኛ ማድረግ የሆነ ሰው፣ ራሱን ለመካድና ጌታ ሲጠራው መስዋዕትነትን ለመክፈል የመጀመሪያው ሰው ይሆናል። ሰው “በልቡ እንዳሚያስብ እንደዚሁ ነው።” ብዙ ሐሳቦች የአንድን ቀን ያልጠፈ ታሪክ ይመሰርታሉ፡፡ MYPAmh 95.3