መልዕክት ለወጣቶች
ክርስቲያናዊ ህብረት
የራሳችሁን ድርሻ በቀጥታ ልትወጡት ያለው ጦርነት በየእለቱ ሕይወታችሁ ውስጥ አለ። በፈተና ጊዜ የራሳችሁን ፍላጎቶች በተፃፈው ቃል ጎን ለማስቀመጥና በብርቱ የኢየሱስን ምክር ለመጠየቅ ትፈቅዳላችሁን? ብዙዎች የጸሎት ስብሰባዎችን ወይንም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ከሰማይ የመጣውን መልእክት የሚያስተላልፉበትን ስብሰባዎች ችላ በማለት ዓለማዊ የሙዚቃ ዝግጅትን (ኮንሰርት) ለመካፈል መሄድ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ። ለእናንተ ክርስቶስ እገኛለሁ ባለበት መገኘት ይሻላችኋል። MYPAmh 93.5
የክርስቶስን ቃላት የሚወዱ ከፀሎት ስብሰባዎች ወይንም የእግዚአብሔር መልእክተኛ ዘላለማዊ ጠቀሜታ ያለውን መልእክት እንዲነግር ከተላከበት ስብሰባ አይቀሩም። ኢየሱስ “በስሜ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በተገኙበት በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁ::” ብሏል። የራስህን ደስታ በመምረጥ በረከትን ማጣት ያዋጣሃልን? በእነዚህ ነገሮች ላይ ያለህ ተሳትፎ ባንተ ሕይወትና ባህሪይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ከአንተ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሰዎች ላይ የሚታይ ተፅዕኖ አለው። MYPAmh 93.6
የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ሁሉ በሥራና በእውነት መሆን የሚገባቸውን ሆነው ቢገኙ ኖሮ የክርስቶስ ሐሳብ ይኖራቸውና የእግዚአብሔርን ስራ ይሰሩ ነበር። ራስን የማስደሰት ፈተናን ይቋቋሙና በመንፈሳዊ ስብሰባዎች ክርስቶስን የመገናኘት እድልን ከከንቱ የምድራዊ ደስታ አስበልጠው እንደሚወዱ ያሳዩ ነበር። በዚህን ጊዜ በሌሎች ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ ያሳድሩና የእነርሱን አርአያ እንዲከተሉ ይመሩአቸዋል። MYPAmh 94.1
ድርጊቶች ከቃላቶች የበለጠ ይናገራሉ። ደስታ ወዳዶች የሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ በመገኘት የሚገኘውን ታላቅ በረከት አያደንቁም:: ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ግለሰቦች ልባቸው በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲነካ ተስፋ በማድረግ አብረዋቸው እንዲሄዱ የማነሳሳትን እድልም አያደንቁትም። ከእነዚህ ጋር ወደ ዓላማዊ ስብሰባዎች ማን አብሮ ይሄዳል? እነዚያን ተሰብሳቢዎች ለመባረክ ኢየሱስ በዚያ አይገኝም። ነገር ግን ሰይጣን ወደ አእምሮአቸው ዘላለማዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ነገሮች የሚያጨናንቁ ብዙ ነገሮችን ያመጣል:: ትክክል የሆነውን ነገር ስህተት ከሆነ ነገር ጋር በመቀላቀል ማወዛገብ ለእርሱ ጥሩ አጋጣሚ ነው። MYPAmh 94.2
ዓለማዊ ስብሰባዎችን መሳተፍ ስሜትን ለሚያነሳሱ መደሰቻዎች ፍላጎት ይፈጠርና የግብረገብ ኃይል ይዳከማል። ደስታ ፈላጊዎች የአምልኮ መልክ ይይዛሉ። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር አስፈላጊ ግንኙነት የላቸውም ። እምነታቸው የሞተ ነው፣ መንፈሳዊ ቅንአታቸው ተለይቶአቸዋል። ከክርስቶስ ተለይተው ላሉት በጊዜው ቃልን በመናገር ልባቸውን ለኢየሱስ እንዲሰጡ ለመጎትጎት ሸክም አይሰማቸውም። The Youth’s Instructor, April 23, 1912. par. 8, also inThe Youths’ Instructor, March 30, 1893, par. 7. MYPAmh 94.3