መልዕክት ለወጣቶች
የመስቀል ኃይል
ኢየሱስ ክርስቶስ በሰብዓዊ እጅ የሰብዓዊ ዘርን ለማቀፍ ሰብዓዊነትን የወሰደ ሲሆን በመለኮታዊው እጁ ደግሞ ዘላለማዊ የሆነውን አምላክ ዙፋን ጨበጠ። መስቀሉን በምድርና በሰማይ አማካይ ቦታ ላይ በመትከል እንዲህ አለ:- “እኔ ከምድር ከፍ ከፍ ባልሁ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ ወደ እኔ እስባቸዋለሁ።” መስቀል የስበት ማዕከል እንዲሆን ነበር የታቀደው። MYPAmh 92.3
መስቀሉ ያስፈለገው ለሁሉም ሰዎች ለመናገርና ውስን ሰውን ውስን ካልሆነው አምላክ ጋር ለማገናኘት ኃጢአት ከሰራው ገደል አልፎ ወደ ራሱ ለመሳብ ነበር። ሰው ከኃጢአት ጋር ከፈጠረው ጠንካራ ስምምነት ሊያላቅቀው የሚችለው የመስቀሉ ኃይል ብቻ ነው:: ክርስቶስ ራሱን የሰጠው ኃጢአተኛውን ለማዳን ነው። ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና ኢየሱስን የሚወዱ ከእርሱ ጋር አንድነት ይፈጥራሉ። የክርስቶስን ቀንበር ይሸከማሉ። ይህ ቀንበር እንዲገታቸውና መንፈሳዊ ሕይወታቸውን እርካታ የሌለው የልፋት ሕይወት ለማድረግ አይደለም፤ በፍፁም አይደለም። የክርስቶስ ቀንበር የክርስቲያን ሕይወት የደስታና የፍስሐ መንገድ እንዲሆን የታቀደ ነበር፡፡ ክርስቲያን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ በመስጠት በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ እንዳይጠፋ ማድረጉን በማሰላሰል መደሰት አለበት:: MYPAmh 92.4