መልዕክት ለወጣቶች

136/511

እራስን የመግዛት ኃይል

ባህሪይ በደንብ ሊቀረጽ የሚችለው በልጅነትና በወጣትነት ጊዜ ነው፡፡ እራስን የመቆጣጠር ኃይልን ልናገኝ ይገባል፡፡ በእሳት ዙሪያና በቤተሰብ አንድነት ውስጥ የሚኖሩ ተጽእኖዎች እስከ ዘላለም የሚቆዩ ውጤቶችን አስከትለዋል፡፡ ሰው በሕይወት ጦርነት አሸናፊ ወይንም ተሸናፊ መሆኑን ከማንኛውም የተፈጥሮ ችሎታዎች የበለጠ በልጅነት አመታት የተመሰረቱ ባህሪያት ይወስናሉ፡፡ MYPAmh 90.5

በቋንቋ አጠቃቀም አዛውንቶችና ወጣቶች ከጥድፊያና ትግስት የለሽ ንግግሮች የበለጠ በራሳቸው ውስጥ ቸል ብለው ለማለፍ ዝግጁ መሆናቸው ምናልባትም ስህተት ላይሆን ይችላል፡፡ እነርሱ «ከቁጥጥሬ ውጪ ሆኖብኝ ነበር፤ ደግሞም ያልኩትን ማለቴ አልነበረም፡፡» ብሎ መለመን በቂ ምክንያት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንደዚህ በቀላል አይመለከትም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፡- «በንግግሩ የሚቸኩልን ሰው አይተህ ታውቃለህን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ ሰው ተስፋ አለው፡፡” «መንፈሱን መግዛት የማይችል እንደፈረሰችና አጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡” MYPAmh 90.6

ለሕይወት መታወክ፣ ለልብ ህመምና ሰላም ማጣት ትልቁን ድርሻ የያዘው ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ቁጣ ነው፡፡ የአንዲት ቅጽበት የችኮላ፣ ከውስጥ የገነፈሉና የግድ የለሽነት ቃላቶች የሕይወት ንስሀ ሊያጠፋ የማይችለውን ክፉ ሰርተው ሊያልፉ ይችላሉ፡፡ አቤት እርዳታና ፈውስን ሊያመጡ ይችሉ በነበሩ ሰዎች መጥፎ የችኮላ ቃላት የተሰበሩ ልቦች፣ የተራራቁ ጓደኛሞች እና የተበላሹ ህይወቶች! MYPAmh 90.7

አንዳንድ ጊዜ የስራ መብዛት እራስን መቆጣጠር አለመቻልን ያስከትላል፡፡ ነገር ግን ጌታ የጥድፊያ ሕይወትንና የተወሳሰቡ እንቅስቃሴዎችን እንድንለማመድ አያስገድድም፡፡ ብዙዎች መሐሪ የሆነው የሰማዩ አባታቸው በላያቸው ያላመጣባቸውን ሸክሞች ወደ ራሳቸው ይሰበስባሉ፡፡ እነርሱ እንዲፈጽሟቸው በፍፁም ያላቀዳቸውን ተግባራት በመፈፀም አንዱ ሌላውን በእብደት መልክ ያባርራል፡፡ እጅግ ብዙ ሸክሞችን በመሸከም እራሳችንን ስናጨናንቅና ልባችንንና አእምሮአችንን ስናደክም፣ ስንረበሽ ፣ ስናዝን፣ በመነጫነጭ ስህተትን ስንፈልግ ጌታ የእርሱን ስም እንደማናከብር እንድንገነዘብ ይፈልጋል፡፡ በእርሱ በመታመንና እንደዚሁም ልባችንን ንፁህ ጣፋጭና ርህሩህ አድርገን በመጠበቅ እግዚአብሔር የሚሰጠንን ሀላፊነቶች ብቻ መሸከም አለብን፡፡ MYPAmh 90.8