መልዕክት ለወጣቶች
አሸናፊ ትሆናለህ።
ለእግዚአብሔር ያሉት ገደብ የለሽ አማራጮች ይህንን ሥራ ለራስህ ስትሰራ ሳለ ካንተ ጋር ግንኙነት ባላቸው በብዙዎች ላይ ተፅእኖ እያሳደርክ ነህ። በወቅቱ የተነገሩ ቃላት ምንኛ መልካም ናቸው! ራስን ወደሚያዋርዱ ልምዶች ላዘነበለ ሰው የሚነገር የተስፋ ቃል ምን ያህል ጥንካሬ፣ ድፍረትና በትክክለኛ አቅጣጫ ውሳኔ የማድረግ አቅም ይሰጥ ይሆን! ጥሩ መርሆዎችን ለመተግበር ያለህ ፅኑ ዓላማ ነፍሳት በትክክለኛ አቅጣጫ ሚዛን እንዲጠብቁ ይረዳቸዋል። MYPAmh 83.8
ማድረግ ስለምትችለው መልካም ነገር ገደብ የለውም። የእግዚአብሔርን ቃል የሕይወትህ መርህ ብታደርግ፣ ተግባሮችህን በቃሉ ብትቆጣጠር፣ እንደዚሁም ተግባርህን በመፈፀም ሂደት ዓላማዎችህና ጥረቶችህ ለሌሎች በረከት እንጂ መርገም ካልሆኑ ጥረቶችህ በክንውን ይጠናቀቃሉ። ራስህን ከእግዚአብሔር ጋር አገናኝተሃል፤ ለሌሎች የብርሃን መተላለፊያ መስመር ሆነሃል። ከኢየሱስ ጋር አብሮ ሠራተኛ የመሆንን ክብር አግኝተሃል:: “አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” በማለት ከአዳኙ ከንፈሮች ከሚወጡ የተባረኩ ቡራኬዎች የበለጠ ክብር የትም አታገኝም፡፡ The Youth’s Instructor Sept.1, 1886. MYPAmh 84.1