መልዕክት ለወጣቶች

119/511

ከክርስቶስ ጋር አንድነት

በሕያው እምነት ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ዘለቄታ ያለው ነገር ነው። እያንዳንዱ ሌላ አንድነት መጥፋት አለበት። ክርስቶስ በመጀመሪያ ለደህንነታችን ስፍር የለሽ ዋጋ በመክፈል መረጠን። ስለዚህ እውነተኛ የሆነ አማኝ ክርስቶስን የመጀመሪያ፣ የመጨረሻና ከሁሉም ነገር የሚበልጥ አድርጎ ይመርጠዋል። ነገር ግን ይህ አንድነት የሚያስከፍለን ነገር አለ። ይህ አንድነት ኩሩ ከሆነ ፍጥረት ጋር ሊደረግ ያለ ሙሉ በሙሉ በሌላው ላይ መደገፍን የሚጠይቅ ህብረት ነው። ይህንን አንድነት የሚመሠርቱ ሁሉ የክርስቶስ የስርየት ደም እንደሚያስፈልጋቸው ሊሰማቸው ይገባል። የልብ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት አለባቸው:: ከውስጣዊና ከውጫዊ እንቅፋቶች ጋር ትግል ሊኖር ይችላል። አስጨናቂ የሆነ ከአንዱ የመለየትና ከሌላው ጋር የመጣበቅ ሥራ ሊኖር ይገባል:: ከክርስቶስ ጋር አንድነት መፍጠር ካለብን ኩራት፣ ራስ ወዳድነት፣ ከንቱነት፣ ዓለማዊነት፣ በጥቅሉ ኃጢአት በሁሉም መልኩ መሸነፍ አለበት። ብዙዎች የክርስትና ሕይወትን እጅግ ከባድ አድርገው የሚያዩበት ምክንያት በውስጣቸው ካሉ ከሚወዱአቸው ጣኦቶቻቸው ሳይለዩ ራሳቸውን በክርስቶስ ላይ ማጣበቅ(ማያያዝ) ስለሚፈልጉ ነው። MYPAmh 79.1

አንዴ ከክርስቶስ ጋር ህብረት ከተመሰረተ በኋላ ፀንቶ ሊቆይ የሚችለው ልባዊ በሆነ ፀሎትና በማያቋርጥ ጥረት ነው። ራስን መቋቋም፣ መካድና ማሸነፍ አለብን። በክርስቶስ ፀጋ፣ በድፍረት፣ በእምነት፣ ነቅቶ በመጠበቅ ድልን ማግኘት እንችላለን።—Testimonies for the Church 5:231. (120) MYPAmh 79.2