መልዕክት ለወጣቶች
ከፍ ላለ ፍፃሜ መጠራት
እነሆ ወጣቶች የተጠሩለትን ከፍ ያለ ፍፃሜ ምነው ማድነቅ በቻሉ! እግሮችህ የሚሄዱበትን መንገድ በደንብ አሰላስል:: ሥራህን ከፍ ባለና ቅዱስ ዓላማ ጀምር:: እንደዚሁም በእግዚአብሔር ፀጋ ኃይል ከጽድቅ መንገድ ላለመመለስ ወስን:: በተሳሳተ አቅጣጫ መጓዝ ብትጀምር እያንዳንዱ እርምጃህ በአደጋና በጥፋት የታጠረ ይሆናል:: በመሆኑም ከእውነት ፣ ከደህንነትና ከስኬት መንገድ እየራቅክ ትሄዳለህ:: በእግዚአብሔር ኃይል የአእምሮ ችሎታህ ሊበረታታና የግብረገብ ኃይሎችህ ሊነቃቁ ይገባል:: MYPAmh 22.3
የእግዚአብሔር ሥራ የኛነታችንን እጅግ ከፍ ያሉ (የከበሩ) ኃይሎች ይፈልጋል:: በብዙ የሥራ መስኮች ጊዜ የማይሰጥ የተማሩ ወጣቶች ፍላጎት አለ:: አሁን ለመከር በተዘጋጁ ሰፊ የስራ መስኮች ለመስራት የሚታመኑ ሰዎች ያስፈልጋሉ:: ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር የሰጡና በክፉ ሥራና በሃጢአት ያልረከሱ ተራ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የተሳካላቸውና የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ ለመፈፀም ገጣሚዎች እንዲሆኑ ይደረጋሉ:: ወጣቶች ተግሳፅን የሚሰሙና አስተዋይ አእምሮ ያላቸው ይሁኑ:: MYPAmh 22.4
እግዚአብሐየር የሰጣቸውን ብርታት በጅልነትና በስካር ያባከኑ ወጣቶች እንዴት ብዙ ናቸው! ከንቱ ልምዶችን ከመፈፀማቸው የተነሳ በአእምሮ፤ በግብረገብና በአካላቸው ጉዳት የደረሰባቸው የስንቶቹ አሳዛኝ ታሪኮች ናቸው በፊቱ የተገለጡት! ሕገወጥ ደስታን በመሻት በመጠመዳቸው የተፈጥሮ የአካል ጤናቸውና ብርታታቸው ክፉኛ ተጎድቷል፤ የህይወታቸው ጠቃሚነትም እጅግ ቀንሷል:: MYPAmh 22.5
የዘመኑን ግድየለሾችና ጥንቃቄ የጎደላቸውን ወጣቶች እንድትለወጡና ከእግዚአብሔር ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ አደፋፍራችኋለሁ:: ሌሎችን መባረክና ማዳን የህይወታችሁ ጥናት ይሁን:: ከእግዚአብሔር እርዳታን ብትሹ በናንተ ውስጥ የሚሰራው የእግዚአብሔር ኃይል ተቃዋሚ ኃይሎችን ሁሉ ከንቱ ያደርጋቸውና እናንተ በእውነት ትቀደሳላችሁ:: በዘመኑ ወጣቶች መካከል ኃጢአት በአስደንጋጭ ሁኔታ ይታያል:: ነገር ግን ነፍሳትን ከሰይጣን ኃይል ነፃ ለማውጣት ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ የናንተ ዓላማ ይሁን:: MYPAmh 22.6