መልዕክት ለወጣቶች
ቅድስና ቀጣይነት ያለው ልምምድ
ቅድስና ቀጣይነት ያለው ልምምድ ነው። እነዚህ ቀጣይነት ያላቸው ደረጃዎች በሐዋሪያው ጴጥሮስ ቃላት እንደሚከተለው ተገልፀዋል። “ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፣ በበጎነትም እውቀትን፣ በእውቀት ላይ መሻትን መግዛት፣ መሻትን በመግዛት ትዕግስትን፣ በትዕግስት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፣ እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ የወንድማማች ፍቅርን ጨምሩ:: እነዚህ ነገሮች በእናንተ ውስጥ ቢሆኑና ቢበዙላችሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ባዶ ወይም ፍሬ ቢስ አትሆኑም።” “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ ትጉ:: እነዚህን ነገሮች ካደረጋችሁ በፍፁም አትወድቁም። ወደ ጌታችንና ወደ አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግስት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።” MYPAmh 77.3
በፍፁም እንደማንወድቅ ማረጋገጫ የሚሰጠን መንገድ እዚህ ይገኛል። የክርስቲያን ፀጋዎችን ለማግኘት በመደመር እቅድ ላይ እየሰሩ ላሉ እግዚአብሔር የመንፈሱን ሥጦታዎች ሊሰጣቸው የብዜት እቅድ እንደሚሰራላቸው ማረጋገጫ አለላቸው። MYPAmh 77.4
ጴጥሮስ ውድ እምነት ላላቸው ሲናገር “እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ።” ብሏል። በመለኮታዊ ፀጋ ፈቃድ ውስጥ የሆኑ ሁሉ በመጨረሻ “በመዝሙርና በዘላለማዊ ደስታ” ያንን ከምድር ወደ ሰማይ የሚደርሰውን መሰላል አንፀባራቂ ደረጃዎች ይወጡና ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይገባሉ። Review & Herald, Nov.15, 1887. MYPAmh 77.5