መልዕክት ለወጣቶች

114/511

ቅድስና የየዕለቱ ሥራ

ቅድስና የየዕለቱ ሥራ ነው። እግዚአብሔር ከመስፈርቶቹ አንዱን እየጣሱ እያሉ ይቅር ይለናል፣ ይባርከናልም በሚል እምነት ማናቸውም ራሳቸውን አያታልሉ። የታወቀ •ኃጢአትን በራስ ፈቃድ መፈፀም የመንፈስ ቅዱስን የምስክርነት ድምፅ ፀጥ ያደርግና ነፍስን ከእግዚአብሔር ይለያል። የኃይማኖታዊ ስሜት ፍስሐ ምንም ቢሆን መለኮታዊውን በግ በማያከብር ልብ ውስጥ ኢየሱስ መኖር አይችልም። እግዚአብሔር የሚያከብሩትን ብቻ ያከብራቸዋል። MYPAmh 76.5

“ለመታዘዝ ራሳችሁን ለምታስገዙለት ለዚያ ለምትታዘዙለት ለርሱ ባሪያዎች ናችሁ።» የምንቆጣ ከሆንን፣ ፍትዎት፣ መመኘት፣ ጥላቻ፣ ራስ ወዳድነት ወይንም ማንኛውም ዓይነት ኃጢአት ካለብን የኃጢአት ባሪያዎች እንሆናለን:: “ማንም ሰው ሁለት ጌቶችን ማገለገል አይችልም።» ኃጢአትን ካገለገልን ክርስቶስን ማገልገል አንችልም። ክርስቲያን የኃጢአትን ፍላጎት ያውቃል። ምክንያቱም ሥጋ በመንፈስ ላይ ይቀናል፤ ነገር ግን መንፈስ የማያቋርጥ ጦርነት በመግጠም ሥጋን ለማሸነፍ ይጥራል። MYPAmh 76.6

በዚህ ቦታ ነው የክርስቶስ እርዳታ የሚያስፈልገው:: ሰብዓዊ ድክመት ከመለከታዊ ጥንካሬ ጋር ይጣመርና እምነት “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ማሸነፍ ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምሥጋናይሁን” በማለት ይናገራል። MYPAmh 76.7

እግዚአብሔር የሚቀበለውን ባህሪይ ማጎልበት ካለብን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ትክክለኛ ልምዶችን መመሥረት አለብን። ሥጋዊ ምግብ ለአካል ደህንነት አስፈላጊ የሆነውን ያህል የየዕለቱ ፀሎትም ለመንፈሳዊ ሕይወትና በፀጋ ለማደግ አስፈላጊ ነው። በፀሎት አስተሳሰባችንን ወደ ላይ ማንሳትን ራሳችንን ማለማመድ አለብን። አእምሮ ሲባዝን መልሰን ማምጣት አለብን። በማያቋርጥ ጥረት በመጨረሻ ልምድ ቀላል ያደርገዋል። ለአንድ አፍታ እንኳን ቢሆን በሰላም ራሳችንን ከክርስቶስ መለየት አንችልም:: የእርሱ መገኘት በእያንዳንዱ እርምጃችን ሊከተለን የሚችለው እራሱ ያስቀመጣቸውን ሁኔታዎች በመጠበቅ ነው። MYPAmh 76.8