መልዕክት ለወጣቶች
በስሜታችሁ አትታመኑ
አንዳንድ ጊዜ የእኛ ዋጋ ቢስነት ስሜት የፍርሃት ንዝረትን በነፍስ ውስጥ ይለቃል። ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው አቋም ወይም እኛ ለእግዚአብሔር ያለን አቋም ተለውጧል ማለት አይደለም። ትናንት የተሰማን ደስታና ሰላም ዛሬ ላይሰማን ይችላል። ነገር ግን በእምነት የክርስቶስን እጅ መያዝና በብርሃን ጊዜ እንደምናደርግ ሁሉ በጨለማ ጊዜም በእርሱ መታመን አለብን። MYPAmh 75.4
ሰይጣን ክርስቶስ ሊያድንህ እስከማይችል ድረስ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ሊያሾከሹክ ይችላል። በርግጥ ኃጢአተኛና ያልተገባህ መሆንህን ብትቀበልም ፈታኙን በክርስቶስ የማስተሰረይ ሥራ «ክርስቶስ አዳኜ እንደሆነ አምናለሁ። በራሴ መልካም ሥራ አልታመንም። ነገር ግን ከኃጢአቴ ሊያነፃኝ በሚችል በክርስቶስ የከበረ ደም እታመናለሁ:: አሁኑኑ ረዳት የለሽ ነፍሴን በክርስቶስ ላይ አንጠለጥላለሁ::» በሚል ጩኸት ፈታኙን ልትጋፈጠው ትችላለህ። የክርስቲያን ሕይወት የማያቋርጥ ሕያው እምነት የሚገለፅበት መሆን አለበት። ተስፋ የማይቆርጥ መታመን፣ በክርስቶስ ላይ የሚደረግ ፅኑ መደገፍ ለነፍስ ሰላምና ማረጋገጫ ያመጣል። MYPAmh 75.5