መልዕክት ለወጣቶች

92/511

መታመንን ማጎልበት

እግዚአብሔር እናንተ እንድትደርሱ የሚፈልግባችሁን ከፍ ያለ ደረጃ ለመድረስ የምታደርጉትን ጥረት እውቅና ይሰጠዋል፡፡ ጥረታችሁ ሳይሳካ ሲቀር፣ ለኃጢአት አልፋችሁ ስትሰጡ መፀለይ እንደማትችሉና በጌታ ፊት ለመምጣት ብቃት እንደሌላችሁ አይሰማችሁ፡፡ «ልጆቼ ሆይ ኃጢአት እንዳትሰሩ ይህንን እጽፍላችኋለሁ፡፡ ከእናንተ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራ በአብ ዘንድ ፃዲቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አለ፡፡» የጠፋውን ልጅ ለመቀበል እጆቹን ዘርግቶ ይጠብቃል፡፡ ወደ እርሱ ሂዱና ስለ ስህተታችሁና ስለ ውድቀታችሁ ንገሩት:: አዲስ ጥረት እንድታደርጉ እንዲያበረታችሁ ጠይቁት:: እርሱ በፍፁም ተስፋ አያስቆርጣችሁም፤ መታመናችሁንም ከንቱ አያደርገውም፡፡ MYPAmh 67.1

ፈተና ይመጣባችኋል፡፡ በመሆኑም ጌታ በባህሪያችሁ ውስጥ ያለውን ሸካራነት ይሞርደዋል፡፡ አታጉረምርሙ፡፡ ስታማርሩ ፈተናውን የበለጠ ታጠነክራላችሁ፡፡ በደስታ በተሞላ ራስን መስጠት እግዚአብሔርን አክብሩ፡፡ የሚመጣባችሁን ግፊት (ጫና) በትዕግስት ተሸከሙት፡፡ ብትበደሉ እንኳን የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባችሁ ያዙት፡፡ «ምላሳችሁን ከክፉ ከንፈሮቻችሁንም ሽንገላ ከመናገር ጠብቁ፡፡ ከክፉ ራቁ፣ መልካምንም አድርጉ፡፡ ሰላምን እሹ፣ ተከተሉአትም፡፡ የእግዚአብሔር ዓይኖች በፃድቃን ላይ ናቸው፤ ጆሮዎቹም ጩኸታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፡፡» MYPAmh 67.2

«አደገኛ ከሆኑ እርምጃዎች ተጠንቀቁ፣ •እጅግ የጨለማውን ቀን ከታገሳችሁት ነገ ያልፋል፡፡» «በፀጥታና በመታመን ብርታታችሁ ይሆናል፡፡» ክርስቶስ የፈተናችሁን ጥንካሬና የእናንተንም የመቋቋም ኃይል ያውቃል፡፡ ለእያንዳንዱ በመከራ ውስጥ ላለ ልጅ ርህራሄ በተሞላ ሐዘኔታ እጆቹ ሁል ጊዜም የተዘረጉ ናቸው፡፡ ለተፈተናና ተስፋ ለቆረጠው እንዲህ ይላል፡፡ «መከራ ተቀብዬ የሞትኩልህ ልጄ ልትታመንብኝ አትችልምን?” «እንደቀኖችህ እንዲሁ ብርታትህ ይሆናል፡፡” MYPAmh 67.3

«መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ ፣ በእርሱም ታመን እርሱም ያከናውንልሃል፡፡» እርሱ ላንተ በሐሩር ምድር እንደ ታላቅ አለት ጥላ ይሆንልሃል፡፡ እንዲህ ይላል፡- «ወደ እኔ ኑ …. እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ፡፡” እርሱ የሚሰጠው እረፍት ዓለም ሊሰጥም ሆነ ሊወስድብን የማይችለው እረፍት ነው፡፡ MYPAmh 67.4

እግዚአብሔርን በቃሉ የሚይዝ ሰው ያለውን ሰላምና ደስታ ቃላት ሊገልፁት አይችሉም:: ፈተናዎች አይረብሹትም፣ ሌሎች ቢያቀልሉትም አይቆጣም፡፡ እኔነት ተሰቅሏል፡፡ ከቀን ወደ ቀን የሥራ ጫና እየጨመረ ሊመጣ ይችላል፣ ፈተናዎቹ እየጠነከሩ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ፈተናዎቹ የበለጠ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከፍላጎቱ ጋር እኩል የሆነ ብርታት ስለሚያገኝ ተስፋ አይቆርጥም፡፡ The youth Instructor, June 26,1902. MYPAmh 67.5