መልዕክት ለወጣቶች

83/511

በራስ መታመንና እውርነት

የተታለሉ ወጣቶች ዓይን ቢከፈት ኖሮ ነፍሳትን በማጥፋት ባገኘው ክንውን ሰይጣን በተንኮል ሥራው ከፍ ከፍ ሲል ያዩት ነበር፡፡ ሊታሰብ በማይቻል መንገድ ሁሉ ሊያጠምዳቸው የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለመያዝ ፈተናዎቹን ለተለያዩ ሁኔታዎች ገጣሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ይሻል፡፡ እያንዳንዱን ወጥመድ ይሞክራል፤ ለነዚህ ፈተናዎች የተጋለጡት እግዚአብሔርን ካልፈለጉ በስተቀር የራሳቸውን ሁኔታና አደጋ ባለ ማወቅ ለማታለያዎቹ •እውራን ይሆናሉ፤ በራሳቸው የሚታመኑና በራሳቸው ብቃት የሚኮሩ ይሆናሉ፡፡ በሆነ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠውን እምነት ወደ መናቅ ፈጥነው ይመጣሉ፡፡ MYPAmh 61.5

ለወጣቶች እንደሚያውቅና በመንገዳቸው ላይ የሚጠብቃቸው አደጋ እንደ ተገለጠለት ሰው እናገራለሁ፡፡ በራስ መተማመን ወደ ጠላት ወጥመድ ይመራችኋል፡፡ ወጣቶች ከእግዚአብሔር ምክር አይጠይቁም፤ ለወጣቶች እንደሚያውቅና በመንገዳቸው ላይ የሚጠብቃቸው አደጋ እንደ ተገለጠለት ሰው እናገራለሁ፡፡ በራስ መተማመን ወደ ጠላት ወጥመድ ይመራችኋል፡፡ ወጣቶች ከእግዚአብሔር ምክር አይጠይቁም፤ እርሱን ምሽጋቸውና ብርታታቸው አያደርጉትም፡፡ ከማሰብ ችሎታቸው የተነሳ ለራሳቸው እውነትን ማግኘት የሚችሉ ይመስል በሙሉ እርግጠኝነት፣ ትክክል የሆነውን ለመምረጥና የእግዚአብሔርን ምስጢሮች ለማስተዋል እንደሚችሉ በማሰብ ወደ ሕብረቱ ይገባሉ፡፡ MYPAmh 61.6

ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ በጣም የምንፈራው በራሳቸው ለሚተማመኑት ነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔርና የሰው ጠላት ባዘጋጀው መረብ ውስጥ በእርግጠኝነት ስለሚጠመዱ ነው፡፡ አንዳንድ እንደ ቅርብ ወዳጅ የተመረጡና በጥርጣሬ ስህተት የተበከሉ በነዚህ ወገኖች አእምሮ የሰይጣንን ያለ ማመን እርሾ ይተክላሉ፡፡ ለማሞኘት በታቀደ የመክሊት ሙገሳ፣ በእውቀት ትልቅነታቸው፣ ለከፍተኛ ሥልጣን ፍላጎትን በውስጣቸው በመቀስቀስ ትኩረታቸውን ይስብና የሞራል ዋግ በላያቸው ያርፋል፡፡ በራሳቸው አስተሳሰብ ከፍ ከፍ ያሉ ለደህንነታቸው የተሰዋውን የአዳኙን ደም ይንቃሉ፤ የፀጋ መንፈስንም ይንቃሉ፡፡ MYPAmh 62.1

ታላቅ ብርሃን የነበራቸውና እውነተኛ ፍላጎት ያሳዩ የነበሩ የሰንበት ጠባቂ ወላጆች ልጆች የሐፍረት ውርስ ትተው የሚያልፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነርሱ ነፋስን የሚዘሩና አውሎ ንፋስን የሚያጭዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የተሰጣቸውን ታላቅ ብርሃን በመናቅ ኃጢአት የሰሩ ሰዎች ስም ከጌታ ፊትና ከኃይሉ ግርማ ለመለየት ከተፈረደባቸው ጋር በፍርድ መዝገብ ይጻፋል:: እነርሱ ይጠፋሉ፤ ይጠፉና የክርስቶስ ፀጋ ላይ ካፌዙ ጋር ይቆጠራሉ፡፡ MYPAmh 62.2

ልጆቼ ወደ ሞት በሚያመራው መንገድ ላይ ሲሄዱ ከማይ ሞተው ተቀብረው ባያቸው ይሻለኛል፡፡ ልጆች የሰማይን አምላክ እንዲዋጉ፣ በመጨረሻ ዘመን የከሃዲያን ቁጥር ከፍ እንዲልና በሰይጣን ጥቁር ባንዲራ ሥር እንዲሰለፉ የማሰልጠን እውነታ በርግጥ ለኔ ፍርሃት የሚለቅብኝ ሐሳብ ነው፡፡ MYPAmh 62.3