መልዕክት ለወጣቶች

77/511

አለ አስፈላጊ ፈተናዎችን መሸሽ አለብን

«ከምትችሉት በላይ በሆነ ፈተና ውስጥ እንድትፈተኑ ዝም የማይል እግዚአብሔር ታማኝ ነው፡፡ ነገር ግን ፈተናውን እንድትቋቋሙት ከፈተናው ጋር መውጫን ያዘጋጅላችኋል፡፡» እኛም የራሳችን ድርሻ ይኖረናል፡፡ ራሳችንን አላስፈላጊ በሆነ ፈተና ውስጥ ማስገባት የለብንም:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- «ከመካከላቸው ውጡ፣ ተለዩ፣ እርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፡፡ እኔም እቀበላችኋለሁ፣ አባትም እሆናችኋለሁ፣ እናንተም ወንድና ሴት ልጆቼ ትሆኑኛላችሁ፡፡” ደስታን ለማግኘት ስንል ከዓለማውያን ጋር ህብረት ከፈጠርን፣ ከዓለማዊ ልምምዶች ጋር ራሳችንን ካስማማን፣ ፍላጎታችንን ከማያምኑ ጋር ካስተባበርንና እግሮቻችንን በፈተናና በኃጢአት መንገድ ላይ ካደረግን እግዚአብሔር ከመውደቅ እንዲጠብቀን እንዴት ተስፋ እናደርጋለን? MYPAmh 59.2

ራሳችሁን ከሚያረክሱ የዓለም ተጽእኖዎች አርቁ፡፡ የጠላት ኃይሎች በብርቱ ወደ መሸጉበት ስፍራዎች ሳትጠሩ አትሄዱ፡፡ MYPAmh 59.3

ወደ ምትፈተኑበትና ወደ ስህተት ልትመሩ ወደምትችሉበት ቦታ አትሂዱ ፡፡ ነገር ግን ለማያምኑ ሰዎች መልእክት ካላችሁና ከእግዚአብሔር ጋር እጅግ የተቀራረባችሁ ሆናችሁ ለእነርሱ በወቅቱ ቃልን መናገር የምትችሉ ከሆናችሁ ያኔ እነርሱን የሚጠቅምና እግዚአብሔርን የሚያስከብር ሥራ መሥራት ትችላላችሁ፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፡- «ከዓለም እንድታወጣቸው አልጸልይም፣ ነገር ግን ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ፡፡” Review and Herald, April 14,1904. MYPAmh 59.4