መልዕክት ለወጣቶች
መግቢያ
ባህርይን ለዘላለም መገንባት
ለወጣቶች ጥልቅ ፍላጎት ስላለኝ የክርስቲያን ባህሪያትን ለመገንባት ቃሉን ተግተው በማጥናትና ልባዊ በሆነ ፀሎት በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችል ሥልጠና እንዲኖራቸው ሲጥሩ ለማየት እጅግ እጓጓለሁ:: እጅግ ከፍ ወዳለው ክርስቲያናዊ ልምምድ ለመድረስ እርስበርስ ሲረዳዱ ለማየት እጓጓለሁ:: MYPAmh 18.1
ክርስቶስ የመዳን መንገድ በመሆን ሰብዓዊ ዘርን ለመድረስ መጣ:: በዚህም የደህንነትን መንገድ ትንሽ ህፃን እንኳን ሊሄድበት እንዲችል አድርጎ አስተካከለው:: ተከታዮቹን ጌታን ለማወቅ እንዲከተሉት ይጠይቃል:: እነርሱም በየቀኑ የእርሱን አመራር ሲከተሉ አወጣጡ እንደ ንጋት የተዘጋጀ መሆኑን ይማራሉ:: MYPAmh 18.2
ማለዳ የፀሐይን መውጣትና ቀስ በቀስ በምድርና በሰማይ ላይ ሙሉ የቀን ብርሃን ሲሆን አይታችኋል:: ቀስ በቀስ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ንጋት ይጨምራል:: ከዚያም እስከ እኩለ ቀን ሙሉ ግርማ እስኪደርስ ድረስ ብርሃኑ ያለማቋረጥ እየጨመረ” እየጠነከረና እየጠራ ይሄዳል:: ይህ እግዚአብሔር የልጆቹን ክርስቲያናዊ ልምምድ ፍፁም ለማድረግ ያለው ፍላጎት ውብ መግለጫ ነው:: እርሱ የሚፈለግብንን ሁሉ ለማድረግ በፍላጎታችን በመታዘዝ በየቀኑ በሚልክልን ብርሃን ስንሄድ ክርስቲያናዊ ልምምዳችን በክርስቶስ የሱስ ሙሉ ሰዎች ወደ መሆን እስክንደርስ ድረስ እያደገና እየሰፋ ይሄዳል:: MYPAmh 18.3
ወጣቶች ሁል ጊዜ የሱስ የተከተለውን መንገድ በፊታቸው ማኖር ያስፈልጋቸዋል:: ክርስቶስ በያንዳንዱ እርምጃ የሄÅበት መንገድ የድል መንገድ ነበር:: ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው ህዝቦችን ለመግዛት ንጉስ ሆኖ አልነበረም:: •እርሱ የመጣው ትሁት ሰው ሆኖ ለመፈተንና ፈተናን ለማሸነፍ እንዲሁም እኛ እግዚአብሔርን ለማወቅ መከተል የሚገባንን መንገድ ለመከተል ነበር:: MYPAmh 18.4
የየሱስን ህይወት ስናጠና እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ለልጆቹ ምን ያህል እንደሚያደርግልን እንማራለን:: እንደዚሁም ፈተናዎቻችን የፈለገውን ያህል ትልቅ ቢሆኑም የሱስ ለኛ ከተሸከመው መከራ እንደማይበልጡ እንማራለን:: መንገድ ” እውነትና ህይወትም እርሱ መሆኑን እንድናውቅ ይረዱናል:: ከእርሱ የሕይወት ምሳሌ ጋር የተጣጣመ ህይወት በመኖር ለኛ የከፈለውን መስዋዕትነት ማድነቃችንን ማሳየት ይጠበቅብናል:: MYPAmh 18.5
ወጣቶች ሥፍር በሌለው በእግዚአብሔር ልጅ ደም ተገዝተዋል:: አብ ልጁ ይህንን መስዋዕትነት እንዲከፍል የመፍቀዱን መስዋዕትነት ልብ ይበሉ:: የሱስ ህይወቱን ለሰብዓዊ ዘር የየዕለት መስዋዕት አድርጎ ለመስጠት የሰማይን አደባባዮችና ዙፋን ትቶ ሲወጣ የተወውን ሁሉ ልብ ይበሉ፡፡ ፌዝና ልግጫ ደርሶበታል:: ክፉ ሰዎች ሊጭኑበት የሚችሉትን ስድብና ፌዝ ሁሉ ተሸከመ፡፡ ምድራዊ አገልግሎቱ እንደተጠናቀቀም በመስቀል ተሰቅሎ ሞቷል:: እጆቹና እግሮቹ በምስማር ሲቸነከሩ፤ ሊያድናቸው ከመጣላቸው ሰዎች የሚደርስበት ፌዝና ድብደባ፣ አባቱ ፊቱን ሲያዞርበት በመስቀል ላይ የደረሰበትን ህመምና ሥቃይ አስታውሱ:: ነገር ግን የሱስ ይህንን ሁሉ በማድረግ ፈቃደኛ ለሆኑ ሁሉ የአምላክን ህይወት በሚያክል ዋጋ ህይወት እንዲያገኙ አስቻለ:: MYPAmh 18.6