መልዕክት ለወጣቶች

61/511

ራስን ሙሉ በሙሉ ቀድሶ የመስጠት ውጤቶች

የእግዚአብሔር ፀጋ ልብን ሲቆጣጠር ክፉን ለማድረግ በውርስም ሆነ በልምምድ ያገኘናቸው ዝንባሌዎች መሰቀል እንዳለባቸው ታይቷል፡፡ በነፍስ ውስጥ አዲስ ሕይወት በአዲስ ኃይል የቁጥጥር ሥራ መጀመር አለበት፡፡ የተደረገው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር መደረግ አለበት፡፡ ይህ ሥራ ውስጣዊውንም ሆነ ውጫዊውን ሰው ያጠቃልላል፡፡ ሁለመናችን፣ አካላችን፣ ነፍሳችንና መንፈሳችን የጽድቅ መሳሪያ ለመሆን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር መሆን አለበት፡፡ MYPAmh 51.3

የተፈጥሮ ሰው ለእግዚአብሔር ህግ ተገዢ አይደለም፡፡ በርግጥ በራሱ መሆንም አይችልም፡፡ ነገር ግን በእምነት የተለወጠ ሰው በየእለቱ የክርስቶስን ሕይወት ይኖራል፡፡ እለት ተእለት የእግዚአብሔር ንብረት መሆኑን ይገነዘባል፤ ያሳያልም፡፡ MYPAmh 51.4

አካልና ነፍስ የእግዚአብሔር ናቸው፡፡ ለዓለም ደህንነት ልጁን ስለ ሰጠ አዲስ የሕይወት ዘመንና ፍፁም መታዘዝ ያለበትን ባሕርይ እንድናጎለብት የምህረት ጊዜ ተሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ከኃጢአት ባርነት አድኖን አዲስና ለአገልግሎት የተለወጠ ሕይወት እንድንኖር አስችሎአል፡፡ MYPAmh 51.5