መልዕክት ለወጣቶች

47/511

የሰይጣን ልዩ ጥረት

በሁሉ አቅጣጫ መጠበቅ እንዳለብንና የሰይጣንን ተንኮልና ወጥመዶቹን በትጋት መቋቋም እንዳለብን እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ ራሱን በብርሃን መልአክ በማስመሰል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን በማታለል ወደ ምርኮው እየመራቸው ነው፡፡ ከሰብአዊ አእምሮ ሳይንስ የሚያገኘው ጥቅም እጅግ ታላቅ ነው፡፡ እዚህ በእባብ በመመሰል የእግዚአብሔርን ሥራ ለማበላሸት ሳይታይ ቀስ ብሎ ተንፏቅቆ ይገባል፡፡ የክርስቶስን ተአምሮችና ሥራዎች ሰብዓዊ ያደርጋቸዋል፡፡ MYPAmh 44.1

ሰይጣን በክርስትና ላይ ግልጽና የድፍረት ጥቃት ቢሰነዝር ክርስቲያኖች በለቅሶና በእንባ በአዳኛቸው እግር ሥር እንደሚመጡና ብርቱና ኃይለኛ የሆነው አዳኝ ያንን ደፋር ጠላት መክቶ እንደሚያባርረው ያውቃል፡፡ ነገር ግን ሰይጣን በብርሃን መልአክ ተመስሎ ብቸኛ ከሆነው ትክክለኛና የብርሃን መንገድ ለማሳት በሰዎች አእምሮ ይሰራል፡፡ የጭንቅላት ቅርጽ ጥናት ፣ የሳይኮሎጂና የአስማት ሳይንሶች ሰይጣን ወደዚህ ትውልድ በቀጥታ የመጣባቸው መስመሮችና የምህረት ደጅ መዝጊያ አካባቢ የሚሰራበት ኃይል መገለጫ ናቸው፡፡ MYPAmh 44.2

ወደ ጊዜው ማብቂያ ስንቃረብ የሰው አእምሮ በቀላሉ በሰይጣን ወጥመዶች ይያዛል፡፡ የተታለሉ ሟቾች በክርስቶስ ሥራና ተኣምራቶች አጠቃላይ መርህ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ይመራቸዋል፡፡ ሰይጣን ሁል ጊዜም ሌሎችን ለማታለል የክርስቶስን ሥራ በማስመሰል የራሱን ኃይል ፍላጎት መመስረት ምኞቱ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ይህን በግልጽና በድፍረት አያደርገውም፡፡ እርሱ ብልሃተኛ ስለሆነ ሥራውን ለመፈፀም ውጤታማ የሆነው መንገድ ምስኪን ወደ ሆነው የወደቀ ሰው በብርሃን መልክ መምጣት ነው፡፡ MYPAmh 44.3

ሰይጣን በምድረ በዳ ወደ ኢየሱስ የመጣው መልከኛ በሆነ ወጣት ሰው መልክ አለዚያም በወደቀ መልአክ መልክ ሳይሆን በንጉሥ መልክ ነበር፡፡ በአፉ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ይዞ ነበር የመጣው፡፡ ሲጠቅስም «ተጽፏል” እያለ ነበር:: በስቃይ ላይ የነበረው አዳኛችንም የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ ተጽፏል እያለ በመጥቀስ ተገናኘው፡፡ ሰይጣን የደከማውንና በሥቃይ ላይ ያለውን የክርስቶስን ሁኔታ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቀመ፡፡ እርሱ የኛን ሰብአዊ ተፈጥሮ ወስዶ ነበር፡፡…. MYPAmh 44.4