መልዕክት ለወጣቶች

489/511

ወላጆችን ማማከር

ወጣቶቻችን ጠቢብ መሆን ያለባቸው መቼ ነው? ይህ ሥራ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው? ልጆች የወላጆቻቸውን ፍርድና ምክር ትተው የራሳቸውን ፍላጎትና ዝንባሌ ማማከር አለባቸው ወይ? አንዳንዶች በወላጆቻቸው ፍላጎትም ሆነ ምርጫ ወይም በሳል ፍርድ ትንሽ ሐሳብ እንኳን ማሳረፍ እንዳይችሉ ለወላጆች ሊኖራቸው የሚገባውን የፍቅር ልብ በር ራስ ወዳድነት ዘግቶባቸዋል። በዚህ ጉዳይ የወጣቶች አእምሮ ሊቀሰቀስ ይገባል። አምስተኛው ትዕዛዝ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበት ብቸኛ ተስፋ ነው። ነገር ግን ቀለል ተደርጎ የተያዘና በአንዳንድ ፍቅረኞች የተተወ ነው። የእናትን ፍቅርና የአባትን ጥንቃቄ ችላ ማለት በብዙ ወጣቶች ላይ በእግዚአብሔር ፊት የተመዘገበ ኃጢአት ነው። MYPAmh 283.4

ከዚህ ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሚፈጸም ታላቁ ስህተት ወጣቶችና ልምድ ያነሣቸው ግለሰቦች ፍቅራቸው እንዲረበሽና የፍቅር ልምምዳቸው ሳንካ እንዲያጋጥመው ስለማይፈልጉ ድብቅ መሆናቸው ነው። ከየአቅጣጫው መታየት ያለበት ጉዳይ የፍቅር ጉዳይ ነው። የሌሎችን ልምድ መውሰድና የረጋ፣ በጥንቃቄ የተሞላ ነገሮችን ማመዛዘን በሁለቱም ወገን ያሻል። ይህ ጉዳይ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ በጣም በቀላል የታየ ጉዳይ ነው። MYPAmh 283.5

ወጣት ወዳጆች ሆይ፣ እግዚአብሔርንና እርሱን የሚፈሩ ወላጆችን በምክራችሁ አሳትፉ። በጉዳዩ ፀልዩበት። ወደ ፊት ሕይወታችሁን ልታጣምሩ የምትሹትን ሰው እያንዳንዱን ስሜት መዝኑ! እያንዳንዱን የፀባይ እድገት በጥንቃቄ ተመልከቱ። ልትወስደው ያለው እርምጃ በሕይወትህ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ እርምጃዎች አንዱ ስለሆነ በችኮላ አታድርግ። ስትወድ በእውርነት አትውደድ። MYPAmh 283.6

የጋብቻ ሕይወትህ ደስተኛ ወይም ያልተጣጣመና ጎስቋላ እንደሚሆን በጥንቃቄ አጥናው:: ጥያቄዎች ይነሱ። ይህ ግንኙነቴ ወደ ሰማይ እንድሄድ ይረዳኛልን? ለእግዚአብሔር ያለኝን ፍቅር ይጨምራልን? በዚህ ሕይወቴ ጠቃሚነቴን ያሰፋዋልን? እነዚህ የተንፀባረቁ ጥያቄዎች ያለ እንቅፋት ከተመለሱ እግዚአብሔርን በመፍራት ወደ ፊት ቀጥል። MYPAmh 284.1

ለወደ ፊት ልትጣመሩ ያሰብካትን ወጣት ፀባይ በትክክል ሳትረዳ ቃል ኪዳን ገብተህ ከሆነ ቃል ኪዳን መጋባታችሁ ልትወዳትና ልታከብራት ከማትችላት ወጣት ጋር የግድ ሕይወትህን እንድታጣምር እንደሚያስገድድህ አድርገህ አትውሰድ። ባልተረጋገጠ የመተጫጨት ቃል ኪዳን ውስጥ እንዴት እንደምትገባ ተጠንቀቅ። ነገር ግን ብዙዎች እንደሚያደርጉት ተጋብቶ ከመፋታት ይልቅ የመተጫጨት ቃል ኪዳን ማፍረስ ይሻላል፤ በጣም ይሻላል:: MYPAmh 284.2