መልዕክት ለወጣቶች

487/511

የተከበረ ፀባይ

ያለ ወላጆችዋ እውቅና ከአንዲት ወጣት ጋር አብሮ የሚደሰትና ወዳጁ የሚያደርጋት ወጣት ለእርሷም ሆነ ለወላጆቿ መልካም እያደረገ አይደለም። በምስጢር ግንኙነቶችና ጨዋታዎች አእምሮዋን ያሸንፍ ይሆናል። ነገር ግን ይህንን በማድረግ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ሊኖረው የሚገባውን ጨዋነት ያጣል። የራሳቸውን ምኞት ለመፈፀም ሲሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይጣጣም ግልጽ ያልሆነ ወይም ድብቅ ተግባር ያከናውናሉ። ይህን በማድረግ ለሚወዱአቸው ወላጆቻቸው ታማኝነታቸውን ይነፍጉና ራሳቸው ለራሳቸው ታማኝ ጠባቂዎች ለመሆን ይሞክራሉ። በዚህ ሁኔታ የሚፈፀሙ ጋብቻዎች ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ናቸው። አንዲትን ልጅ ሥራ የሚያስፈታትና ወላጆቿን መታዘዝና ማክበር እንዳለባት ከሚገልጽ ግልጽና ትክክለኛ ትእዛዝ አእምሮዋን የሚያስት ሰው ለጋብቻ ግዴታዎች ታማኝ የሚሆን አይደለም። MYPAmh 282.2

“ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነፃል?” ለሚለው ጥያቄ መልሱ “ነፍሱን እንደ ቃልህ በመጠበቅ ነው” የሚል መልስ ተሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስን መመሪያው የሚያደርግ ወጣት የደህነንትን መንገድ አይስትም። ይህ የተከበረ መጽሐፍ ማታለልን እንዲተውና ቀና ጠባይ እንዲኖረው እንዲሁም እውነተኛ እንዲሆን ያስተምረዋል። “አትስረቅ” የሚለው ትዕዛዝ በእግዚአብሔር ጣቶች በድንጋይ ጽላት ተጽፏል። ነገር ግን ምን ያህል የፍቅር ሌብነት ውስጥ ውስጡን እየተሰራ ምክንያት ይሰጠዋል። MYPAmh 282.3

ልምድ የሌላትንና ድብቅ ግንኙነቷ ወዴት እንደሚያመራ የማታውቀውን ወጣት ፍቅሯን ሊካፈል በማይገባ ጠባዩ ከወላጆቿ በመለየት የማታለል ግንኙነትን ይቀጥላል። መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱን ታማኝነት የጎደለውን ተግባር ያወግዛል። በሁሉም ሁኔታ ትክክለኛ ሥራን ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስን የወጣትነት ዘመኑ መሪና ለመንገዱ ብርሃን የሚያደርግ ወጣት ትምህርቱን በሁሉም ነገር ይከተላል። ይህ ወጣት ታላቅ መስዋእትነትን የሚያስከፍለውም እንኳን ቢሆን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ከህግ አንዲቷን ወይም ነጥቧን አይተላለፍም። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያምን ከሆነ ጥብቅ ከሆነው የእውነት መንገድ ከተለየ የእግዚአብሔር በረከት በእርሱ ላይ እንደማያርፍ ያውቃል። ምንም እንኳን ለጊዜው የተሳከለት ቢመስልም በእርግጠኝነት የሥራውን ፍሬ ያጭዳል።በዚህ የምድራችን ዘመን ያለወቅቱ በሚፈጸሙና ተገቢ ባልሆኑ ብዙ ግንኙነቶች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ያርፍባቸዋል። እነዚህን ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱስ ግልፅ ባልሆነ አሻሚ ብርሃን ትቶት ቢሆን ኖሮ MYPAmh 282.4

ብዙዎቹ የዘመኑ ወጣቶች ለእርስ በርሳቸው ባላቸው ግንኙነት እየተከተሉ ያሉት መንገድ የበለጠ ይቅር የሚባል ይሆን ነበር። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ መጠይቆች (መስፈርቶች) ግማሽ መንገድ ትዕዛዛቶች አይደሉም። የሐሳብ፣ የቃልና የድርጊት ፍፁም ንፅህናን የሚጠይቁ ናቸው። ቃሉ ለእግራችን መብራት በመሆኑ የሃላፊነትን መንገድ ማንም ሰው መሳት በሌለበት ሁኔታ ስላዘጋጀ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስን ገጾች ማማከርንና ምክራቸውን ማድመጥን ሥራቸው ማድረግ አለባቸው። ሁልጊዜ አሳዛኝ ስህተቶች የሚፈጸሙት ከትዕዛዙ በመለየት ነው:: MYPAmh 282.5