መልዕክት ለወጣቶች

483/511

የተጣሰ መተጫጨት

“ቃል ገብቻለሁና አሁን ቃሌን ማጠፍ እችላለሁን?” ትዪ ይሆናል። መልሴ ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ የሆነ ቃል ገብተሽ ከሆነ በማንኛውም መንገድ ሳትዘገዪ ቶሎ ብለሽ የገበሽለትን ቃል እጠፊና ይህን የችኮላ ቃል እንድትገቢ ላደረገሽ ሞኝ ፍቅር በእግዚአብሔር ፊት ራስሽን ዝቅ በማድረግ ንሰሐ ግቢ። የዚህን ዓይነቱን መሀላ ጠብቅሽ ፈጣሪሽን ከምታዋርጂ እርሱን በመፍራት መሀላሽን ማፍረስ በጣም ይሻላል። MYPAmh 280.2

አስታውሺ፣ ማግኘት የምትችይው ሰማይ እንዳለ ሁሉ መሸሽ ያለብሽ ወደ ጥፋት የሚወስድ የተከፈተ መንገድም አለ። እግዚአብሔር አንድን ነገር ሲል ያንኑ ማለቱም ነው። የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ክፉንና ደጉን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ በከለከላቸው ጊዜ አለመታዘዛቸው ዛሬ በምድራችን ላይ ላለው ዋይታ በር ከፈተ:: ከእግዚአብሔር በተቃራኒ አቅጣጫ ከተጓዝን እርሱም ከእኛ በተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዛል። የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም ደህንነታችን የሚደገፈው እኛ ለፈቃዱ በምንሰጠው መታዘዝ ላይ ነው። ሁሉም መጨረሻ በሌለው ፍቅርና ጥበብ ተመስርተዋል። Testimonies for the Church, Vol. 5, P 361-365. MYPAmh 280.3