መልዕክት ለወጣቶች
የተሳሳተ የተቃራኒ ፆታዎች መቀራረብ
(ከግል ምስክርነት)
በፀባይህ ፅናትና ራስን መካድ ማጣት እንደ አሸዋ የማይንሸራተት ቀና የሆነ የኃይማኖት ልምምድ እንዳይኖርህ የሚያደርግ ክፉ መሰናክል ነው። የአላማ ፅናትና •እውነተኝነት መበረታታት አለባቸው። እነዚህ ጠባያት ለተሳካ የክርስቲያን ሕይወት በጣም አስፈላጊ ናቸው። የነፍስ ንፅህና ካለህ ትክክል ከሆነው ነገር ፍንክች አትልም። ማንኛውም ነገር ከቀጥተኛ የሥራ መስመርህ አያዛንፍህም። ለእግዚአብሔር ታዛዥና እውነተኛ ትሆናለህ። የፍቅርና የመቀራረብ ተፅእኖ ከእውነትና ከተግባርህ ወደ ኋላ አይመልሱህም። ተግባርን ለዝንባሌ አትሰዋም። MYPAmh 277.1
ወንድሜ ሆይ፣ የሕይወት ፍላጎትህን ከአንዲት ልምድ ከጎደላትና ተራ በሆኑ የየእለቱ የሕይወት ተግባሮች ላይ እውቀት ከሚያንሳት ወጣት ጋር አንድ ለመሆን ተስበህ ከሆነ ስህተት እየፈፀምክ ነህ:: ነገር ግን ይህ ጉድለቷ ለእግዚአብሔር ሥራ ካላት አለማወቅ ጋር ሲነፃፀር ትንሽ ነው። ብርሃን አልተሰጣትም ማለት አይደለም:: መንፈሳዊ እድሎቹ ቢኖሯትም ያለ ክርስቶስ መሆኑዋና አሰቃቂ ኃጢአተኛነቷ አልተሰማትም። MYPAmh 277.2