መልዕክት ለወጣቶች
ምክር መፈለግ
እግዚአብሔርን በሚፈሩ ወላጆች የተባረክህ ከሆንክ አማክራቸው:: ተስፋዎችህንና እቅዶችህን ግለጥላቸው፣ የህይወት ልምድ ያስተማራቸውን ትምህርት ከእነርሱ ተማር:: ይህንን በማድረግህ ከብዙ የልብ ጭንቀት ትድናለህ:: MYPAmh 276.3
ከሁሉም በፊት ክርስቶስን አማካሪህ አድርገው። ቃሉን በፀሎት አጥና። ይህንን በመሰለ አመራር ሥር በመሆን አንዲት የሕይወት ጓደኛን የምትመርጥ ወጣት ልትመርጠው የሚገባት ጓደኛ ንፁህ ፀባይና ትክክለኛ የወንድነት ባሕርይ ያለው፣ ትጉህ፣ ለተሻለ ነገር የሚጥር፣ ታማኝ፣ እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ መሆን አለበት። የትዳር ጓደኛን የሚፈልግ ወጣትም በአጠገቡ የምትሆንን፣ የሕይወትን ሸክም ድርሻዋን ለመሸከም ብቁ የሆነችን፣ የእርሷ ተፅዕኖ የሚያስከብረውና የሚያስተካክለው የሆነችና በፍቅርዋ የምታስደስተውን ወጣት ሴት መምረጥ አለበት። MYPAmh 276.4
“መልካም ሚስት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነች:: የባሏ ልብ ይታመንባታል፤ በሕይወቷ ዘመን ሁሉ መልካም ታደርጋለች፣ ክፉም አይደለም። አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ በምላስዋም የደግነት ህግ አለ። የባሏን መንገድ በጥንቃቄ ትመለከታለች፣ የሀኬትንም እንጀራ አትበላም። ልጆቿም ተነስተው አንቺ የተባረክሽ ነሽ ይሏታል። ባሏም ደግሞ እንዲህ ብሎ ያሞግሳታል:- ብዙ መልካም ያደረጉ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉም ትበልጪያለሽ።” የዚህችን ዓይነት ሚስት ያገኘ መልካም ነገርን አገኘ። የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል።” The Ministry of Healing P. 358-359፣ ምሳሌ 31፡1- MYPAmh 276.5