መልዕክት ለወጣቶች

44/511

የክፉ ኃይሎችን የመቃወም ጥሪ

የሰይጣን ሥራ እግዚአብሔርን ከሰዎች የልብ ዙፋን በማውረድ ሰብአዊ ባሕርይን በራሱ በተጣመመ መልክ መቅረጽ ነው፡፡ ክፉ ፍላጎቶችን፣ ያልተቀደሱ ስሜቶችንና ምኞቶችን ይቀሰቅሳል፡፡ እነዚህን ሁሉ ኃይሎች ፣ ክብሮች ፣ ብልጽግናዎችና የኃጢአት ደስታዎች እሰጥሃለሁ ብሎ ያውጃል፡፡ ለዚህ እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጣቸው ነገሮች ታማኝነትን መተውና ህሊናን መሸጥ ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ሰብአዊ አካሎችን በማዋረድ በኃጢአት ባርነት ሥር ያደርጋቸዋል፡፡ MYPAmh 42.3

እግዚአብሔር የክፉ ኃይሎችን እንዲቃወሙ ሰዎችን ይጠራቸዋል፡፡ እንዲህም ይላል፡- «በሟች ሥጋችሁ ኃጢአት እንዲነግስ አትፍቀዱ፤ ለፍትዎቱም አትታዘዙ፤ ብልቶቻችሁንም ለኃጢአት የርኩሰት መሳሪያ አታድርጉ፡፡ ነገር ግን ከሙታን እንደተነሱ ሰዎች ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ብልቶቻችሁንም ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሳሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡” MYPAmh 42.4

የክርስቲያን ህይወት ጦርነት ነው፡፡ «የእኛ ውጊያ ከሰዎች ጋር ሳይሆን በዚህ በጨለማ ዓለም ከሚሰሩ ገዢዎች ፣ከባለ ስልጣናትና ከዚህ ዓለም ኃይሎች ማለትም በሰማይ ካሉት ከእርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው፡፡» በዚህ በጽድቅና በርኩሰት መካከል በሚደረግ ጦርነት አሸናፊዎች መሆን የምንችለው በእግዚአብሔር እርዳታ ብቻ ነው፡፡ የእኛ ውስን ፈቃድ ወሰን ለሌለው ለእግዚአብሔር ፈቃድ መገዛት አለበት፡፡ ሰብዓዊ ፈቃድ ከመለኮታዊ ፈቃድ ጋር መዋሃድ አለበት፡፡ ይህ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ያመጣልናል፤ እያንዳንዱ ጦርነት የእግዚአብሔርን በዋጋ የተገዛ ንብረት ወደ መመለስና በነፍስ ውስጥ የእግዚአብሔርን ምስል ወደ መመለስ ያመራል፡፡ MYPAmh 42.5