መልዕክት ለወጣቶች

463/511

ቃላቶቻችን የእርዳታ ምንጭ

ክርስቲያኖች የሕይወት ልምምድን የሚገልፁ ውድ ምዕራፎችን በተመለከተ የሚያወሩት በጣም ጥቂት ነው። የመናገር መክሊታቸውን ያለ አግባብ በመጠቀማቸው የእግዚአብሔር ሥራ ሽባ ከመሆኑም በላይ እግዚአብሔር ክብሩን አጥቷል። ቅንዓት፣ ክፉ ሐሳብና ራስ ወዳድነት በልባቸው ውስጥ እንደ ከበረ እቃ ቦታ ስላገኙ ቃላቶቻቸው የውስጥ ብልሽታቸውን ያሳያሉ። የክርስቶስን ስም በሚጠሩ ብዙዎች ክፉ አስተሳሰብና ክፉ ንግግር ይዘወተራል። እነዚህ ሰዎች ልጁን ለዓለም የሰጠውን የእግዚአብሔርን በጎነት፣ ምህረትና ፍቅር አይናገሩም። እርሱ ይህንን ካደረገልን የእኛ ፍቅርና አመስጋኝነት መገለጥ የለበትምን? ቃላቶቻችን በክርስቲያናዊ ልምምዳችን ለእርስ በርሳችን እርዳታና ማበረታቻ እንዲሆኑ መጣር የለብንም? ክርስቶስን በእውነት ከወደድነው በቃላቶቻችን እናከብረዋለን። ለእግዚአብሔር ያለንን የአመስጋኝነት ንፁህ ቃላት ሲሰሙ ብዙ ጊዜ የማያምኑ ሰዎች ወደ እምነቱ ይመጣሉ። Review and Herald, January 25, 1898. MYPAmh 269.3