መልዕክት ለወጣቶች

459/511

እውነተኛ የባሕርይ መሞረድ

ለእያንዳንዱ ሰው መብቶች እውቅና እንድንሰጥ ጌታ ይጠይቀናል። የሰዎች ማህበራዊ መብቶቻቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለባቸው። ሁሉም እንደ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች በጥንቃቄና ተገቢ ትምህርት በማግኘት መያዝ አለባቸው። MYPAmh 268.1

ክርስትና ሰውን የከበረ ያደርገዋል። ክርስቶስ ለከሳሾቹ እንኳን ገር ነበር! የእርሱ እውነተኛ ተከታዮች ተመሳሳይ መንፈስን ይገልጣሉ። ጳውሎስ በገዢዎች ፊት ቀርቦ ሳለ ተመልከቱት። በአግርጳ ፊት ያደረገው ንግግሩ የእውነተኛ ትህትናና አሳማኝ የሆነ አንደበተርቱእነት መግለጫ ነበር። የክርስቶስ ወንጌል የተለመደውን የዓለም ትህትናን ሳይሆን ከእውነተኛ የልብ ርህራሄ የሚመነጨውን ትህትና ያደፋፍራል። MYPAmh 268.2

የህይወታችንን ውጫዊ ባሕርያት እጅግ በጥንቃቄ ማሳደግ ቁጡነትን፣ የጭካኔ ፍርድንና ተገቢ ያልሆነ ንግግርን ለመቋቋም በቂ አይደለም። ራስ በነገሰበት እውነተኛ የሆነ የባሕርይ ውበት በፍፁም ሊታይ አይችልም። በልብ ውስጥ ፍቅር መኖር አለበት። ትክክለኛ የሆነ ክርስቲያን ለድርጊት የሚያነሳሳውን ነገር የሚያገኘው ለጌታው በውስጡ ጠልቆ ካለው ልባዊ ፍቅር ነው። ለክርስቶስ ካለው ውስጣዊ ፍቅር የተነሣ ለወንድሞች ራስ ወዳድነት የሌለው ፍላጎት ይመነጫል። ፍቅር ለባለቤቱ ፀጋን፣ ትክክለኛነትን፣ የባሕርይ ውበትን ይሰጣል። ፊትን ያበራና ድምጽ ዝግ እንዲል ያደርጋል። የግለሰቡን ሁለንተናውን ይሞርዳል፣ ከፍም ያደርጋል። The Ministry of Healing, pp. 489, 490, 422. MYPAmh 268.3