መልዕክት ለወጣቶች
የጓደኞች ምርጫ
ወደ ሰማይ የምናደርገውን ጉዞ እጅግ ከባድ ለማድረግ ሰይጣን ብዙ እንቅፋቶችን ስለሚያዘጋጅ ለመንፈሳዊ እድገታችን ምቹ የሆኑ ጓደኞችን መምረጥና ማግኘት የምንችልበትን እያንዳንዱን እርዳታ መጠቀም አለብን። ብዙዎች አካባቢያቸው መሆን እንደሚገባው እንዲሆን ማድረግ ስለማይችሉ ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ነገር ግን በራሳችን ምርጫ ክርስቲያናዊ ባሕርይ ለመመሥረት በማይመች ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን ማስቀመጥ የለብንም። ይህንን እንድናደርግ ጥሪ ሲመጣልን በመጥፎ ተፅዕኖ ሥር ሆነን ሳንበላሽ በክርስቶስ ፀጋ መቆም እንድንችል ሁለት እጥፍ የነቃንና የምንፀልይ መሆን አለብን:: MYPAmh 266.1
ሎጥ እርሱንና ቤተሰቡን ሊከባቸው የሚችለውን የሞራል ተፅዕኖ ከመመልከት ይልቅ በዚያ አካባቢ በመኖር የሚያገኘውን ጊዜያዊ ጥቅም በመመልከት ሶዶምን ለመኖሪያነት መረጠ። ዓለማዊ ነገሮችን በተመለከተስ ያገኘው ጥቅም ምን ነበር? ሀብቱ ሶዶም በጠፋ ጊዜ አብሮ ጠፍቷል፣ ከልጆቹ ግማሾቹም ከተማዋ ስትጠፋ አብረው ጠፍተዋል፣ ሚስቱ በመንገድ ላይ ወደ ጨው አምድ ተለውጣለች፣ እርሱ ራሱ የዳነው ከእሳት ተነጥቆ እንደ ዳነ ሆኖ ነው። ነገር ግን የሶዶም የግብረገብ ብልሽት ከልጆቹ ባሕርይ ጋር የተጠላለፈ በመሆኑ በክፉና በመልካም፣ በኃጢአትና በጽድቅ መካከል መለየት አልቻሉም ነበር።—The Signs of the Times, May 29, 1884. MYPAmh 266.2