መልዕክት ለወጣቶች
ክርስቲያናዊ መግባባትና ትህትና
ክርስቲያናዊ መግባባት በእግዚአብሔር ህዝቦች እጅግ በአነስተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ይገኛል። ይህ የትምህርት ዘርፍ በትምህርት ቤቶቻችን ችላ ሊባል ወይም ሊዘነጋ አይገባም። MYPAmh 259.1
ተማሪዎቻችን እያንዳንዳቸው ከሌሎች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው አቶሞች ሳይሆኑ እያንዳንዳቸው ከሌላው ድር ጋር በመተባበር ልብስ የሚፈጥሩ ማጎች መሆናቸውን መማር አለባቸው። ይህ ትምህርት ከቤት ትምህርት ቤት ውጪ በየትኛውም ዲፓርትመንት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊሰጥ አይችልም:: በቤት ትምህርት ቤት ውስጥ በአግባቡ ቢጠቀሙበት ኖሮ ተማሪዎች የባሕርያቸውን ማህበራዊ ገፅታዎች በየቀኑ ለማሳደግ በከፍተኛ ደረጃ ሊረዱ በሚችሉ መልካም አጋጣሚዎች ተከበዋል። ስለዚህ ደስተኛና ጠቃሚዎች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ባሕርይ ለማሳደግ ጊዜያቸውንና አጋጣሚዎችን የማሻሻል ኃይል በእጃቸው ነው። ራሳቸውን በራሳቸው ውስጥ የሚዘጉና በጓደኝነት ግንኙነት ሌሎችን ለመባረክ ፈቃደኛ የማይሆኑ ሰዎች ብዙ በረከቶችን ያጣሉ! ከእርስ በርስ ጋር በሚፈጠረው ግንኙነት አእምሮዎች እርምትና ማስተዋል ያገኛሉ! በማህበራዊ ግንኙነት የልብ አንድነትንና በሰማይ እይታ አስደሳች የሆነ የፍቅር ከባቢ አየርን ሊፈጥር የሚችል ትውውቅና ወዳጅነት ይፈጠራል። MYPAmh 259.2
በዚህ ሁኔታ የክርስቶስን ፍቅር የቀመሱ ሰዎች ያሏቸውን ማህበራዊ ኃይሎች ቢያሳድጉ ኖሮ በዚህ መንገድ ነፍሳትን ወደ አዳኙ ያመጡ ነበር። ክርስቶስ እጅግ እንደሚመኙት ሀብት፣ ቅዱስና ጣፋጭ ሆኖ እነርሱ ብቻ እንዲደሰቱበት በልብ ውስጥ መደበቅ የለበትም! እንደዚሁም የክርስቶስ ፍቅር የእነርሱን የአእምሮ ዝንባሌ ለሚያሟሉ ብቻ መገለጥ የለበትም ። ተማሪዎች ምንም እንኳን እነዚህ እራሳቸው የመረጡአቸው ጓደኞቻቸው ባይሆኑም በችግር ውስጥ ላሉ የርህራሄ ፍላጎትንና ማህበራዊ ዝንባሌን በመግለፅ ክርስቶስን መምሰልን መማር አለባቸው። ኢየሱስ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ስፍራ ለሰብዓዊ ቤተሰብ የፍቅር ፍላጎትን ገልፆአል። በዙሪያው ደስታ የሚታይበት የርህራሄ ብርሃንንም አብቅሏል። ተማሪዎች የእርሱን ዱካ እንዲከተሉ መማር አለባቸው። ለወጣት ጓደኞቻቸው ክርስቲያናዊ ፍላጎትን፣ ርህራሄን፣ፍቅርን እንዲገልጡና እነርሱን ወደ ኢየሱስ ለመሳብ ጥረት እንዲያደርጉ መማር አለባቸው:: ክርስቶስ በልባቸው ውስጥ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሚያድስ ለዘላለማዊ ሕይወት እንደሚፈስ የውኃ ምንጭ መሆን አለበት። MYPAmh 259.3
በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ክቡር ነገር የተቆጠረው በችግር ጊዜ ለሌሎች የሚደረግ ይህ የፈቃደኝነትና የፍቅር አገልግሎት ነው። ስለዚህ ለእምነታቸው እውነተኛ የሆኑ ተማሪዎች ገና በትምህርት ላይ እያሉ ለእግዚአብሔር ህያው ሚስዮናውያን መሆን ይችላሉ። ይህ ሁሉ ጊዜ ሊወስድ ይችላል! ነገር ግን ለዚህ ስራ የዋለ ጊዜ ተማሪው ለዓለም ክርስትናን እንዴት ማቅረብ እንዳለበት እየተማረ ስለሆነ ትርፋማ ጊዜ ነው። MYPAmh 259.4
ክርስቶስ ከሌሎች ጋር ጓደኝነት መፍጠርን እምቢ አላለም:: ፈሪሳውያንም ሆኑ ቀራጮች ግብዣ ሲጠሩት ተቀብሏል:: በእነዚህ አጋጣሚዎች የተናገረው እያንዳንዱ ቃል ለአድማጮቹ የሕይወት ሽታ ለሕይወት ነበር። የእራት ሰዓቱን ለተጋባዦቹ ፍላጎት ገጣሚ የሆኑ ውድ ትምህርቶችን ለማስተላለፍ ተጠቀመ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከአማኞች ጋርም ሆነ ከማያምኑት ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ራሳቸውን እንዴት ማቅረብ ወይም መምራት እንዳለባቸው አስተማራቸው። Testimonies for the Church, Vol. 6, P. 172-173. MYPAmh 259.5