መልዕክት ለወጣቶች

444/511

ክፍል 14—ማህበራዊ ግንኙነቶች

ክርስትና ወደ ዓለም መድረስ የሚችለው በማህበራዊ ግንኙነት አማካኝነት ነው። መለኮታዊ ብርሃንን ያገኘ እያንዳንዱ ወንድና ሴት እነዚያ ከመልካሙ መንገድ ጋር ትውውቅ የሌላቸው ሰዎች በሚሄዱበት የጨለማ መንገድ ላይ ብርሃን ማብራት አለበት። ማህበራዊ ግንኙነቶች በክርስቶስ መንፈስ በመቀደስ ነፍሳትን ወደ አዳኙ ለማምጣት በተገቢ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው። The Ministry of Healing, P. 496. MYPAmh 257.1