መልዕክት ለወጣቶች

437/511

የበዓል ቀናትን እንዴት ማሳለፍ እንዳለብን

በጉልበት ሥራ ለተሰማሩ ሰዎች መዝናኛ አስፈላጊ ነው! በአእምሮ ሥራ ላይ ተሰማርተው ላሉ ደግሞ የበለጠ አስፈላጊ ነው። በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንኳን ቢሆን አእምሮአችን ሁልጊዜ ያለ መጠን እንዲሰራ ማድረግ ለደህንነታችንም ሆነ ለእግዚአብሔር ክብር አስፈላጊ አይደለም። እንደ ጭፈራ፣ ካርዶችን መጫወት፣ ቼዝ መጫወት፣ ቼኬር መጫወት፣ ወዘተ… ያሉትን መዝናኛዎች ሰማይ የሚነቅፋቸው የመዝናኛ ዓይነቶች ስለሆኑ እኛም ልንደግፋቸው አንችልም፡፡ በዝንባሌአቸው ጠቃሚ አይደሉም፣ ነገር ግን በአንዳንድ ሰዎች አእምሮ ጨዋታዎቹ ወደ ቁማርና ምግባረ ብልሹነት ሊመራ የሚችል ዓይነት ከፍተኛ ስሜትን የማነሳሳት ተፅእኖ አላቸው። እንደ እነዚህ ያሉ ጨዋታዎች በሙሉ በክርስቲያኖች መነቀፍና በእነርሱ ፋንታ ፍፁም ጉዳት የሌላቸው ጨዋታዎች ሊተኩ ይገባል። MYPAmh 252.1

የበዓል ቀናቶቻችንን ዓለማውያን በሚያሳልፉበት መልክ ማሳለፍ የለብንም! ሆኖም ለልጆቻችን አለመርካት ሊፈጥር ስለሚችል ትኩረት ሳይሰጣቸው ማለፍ የለባቸውም። በእነዚህ ቀናት ልጆቻችን ለክፉ ተፅዕኖዎች የመጋለጥ አደጋ ስላለባቸውና በዓለማዊ ደስታዎችና ማነቃቂያዎች ሊበከሉ ስለሚችሉ የእነዚህን አደገኛ የመደሰቻ ዘዴዎችን ቦታ ሊተካ የሚችል ነገርን ለማግኘት ወላጆች ጥናት ያድርጉ ። ልጆቻችሁ የእነርሱን ደስታና መልካም ነገር ችላ እንደማትሉ እንዲገነዘቡ አድርጉ። MYPAmh 252.2

በከተማ ወይም በመንደር የሚኖሩ በርካታ ቤተሰቦች አንድ ላይ በመሆንና አእምሮአቸውንና አካላቸውን ያደከመውን ስራ በመተው የተፈጥሮ ውበት ወደሚታይበት ባህር ዳር ወይም ጥሩ ደን ወደ አለበት ወደ ገጠር አካባቢ ጉዞ ያድርጉ። በዚያ ጠረጴዛዎቻቸውን በዛፎች ሥር ወይም ከሰማይ በታች ክፍት በሆነ ቦታ ዘርግተው ተራና ንፁህ የሆነና ከሁሉም የተሻለውን የፍራፍሬና የአዝእርት ምግቦችን ይመገቡ። በዚያ ቦታ የሚደረገው ብስክሌት መንዳት፣ የአካል እንቅስቃሴና የቦታው ውበት የምግብ ፍላጎታቸውን ስለሚቀሰቅስ ነገስታትን በሚያስቀና ዓይነት ምግብ መደሰት ይችላሉ። MYPAmh 252.3

በእንደነዚህ ዓይነት ጊዜያቶች ወላጆችና ልጆች ከስጋት፣ ከሥራና ከግራ መጋባት ነፃ መሆን አለባቸው:: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ልጆች መሆንና በተቻለ መጠን ለእነርሱ ሁሉም ነገር አስደሳች እንዲሆንላቸው ማድረግ አለባቸው። ቀኑን በሙሉ ለመዝናናት ማዋል አለባቸው:: MYPAmh 252.4

ለቢሮ ሰራተኞችና ብዙ ጊዜ ተቀምጠው ለሚሰሩ ሰዎች ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤናቸው ጠቃሚ ይሆናል። ይህንን ማድረግ የሚችሉ ሁሉ ይህን መንገድ መከተልን እንደ ሃላፊነታቸው አድርግው መውስድ አለባቸው። ምንም የሚጠፋ ነገር አይኖርም፣ ነገር ግን ብዙ ጥቅም ይገኝበታል። ወደ ሥራቸው በቅናት ለመሰማራት አዲስ ህይወትና ድፍረት በማግኘት ይመለሳሉ! በሽታን ለመቋቋምም በተሻለ ሁኔታ የተዘጋጁ ይሆናሉ። Testimonies for the Church, Volume1. p. 514-515. MYPAmh 252.5