መልዕክት ለወጣቶች

421/511

ከዓለም መለየት

እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች መስዋዕት የሚያደርጓቸው ነገሮች ይኖራሉ። በዚያ ቦታ ኢየሱስን ስለማያገኙት የዓለማዊ መደሰቻ ቦታዎችን ይርቃሉ። በዚያ ቦታ ሰማያዊ አእምሮ እንዲኖራቸውና በፀጋ እንዲያድጉ የሚያደርጉአቸው ተፅዕኖዎች ስለሌሉ ከዚያ ይርቃሉ። ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸው ታዛዥነት ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ እንዲወጡና የተለዩ እንዲሆኑ ይመራቸዋል። MYPAmh 242.5

“ከፍሬያቸው ታውቁአቸዋላችሁ።” (ማቴ7፡20) በማለት አዳኙ ተናግሯል። እውነተኛ የሆኑ የክርስቶስ ተከታዮች ለእርሱ ክብር ፍሬ ያፈራሉ። ሕይወታቸው በእግዚአብሔር መንፈስ መልካም ሥራ መሠራቱንና ፍሬያቸውም ለቅድስና መሆኑን ያረጋግጣል። ሕይወታቸው የከበረና ንፁህ ነው። ትክክለኛ ተግባራት የእውነተኛ እግዚአብሔርን የመምሰል ፍሬ ናቸው። እንደዚህ አይነቱን ፍሬ የማያፈሩ በእግዚአብሔር ነገሮች ውስጥ ምንም ልምምድ እንደሌላቸው ይገልጣሉ። እነርሱ በወይኑ ግንድ ላይ አይደሉም። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “በእኔ ኑሩ እኔም በናንተ። ቅርንጫፍ በግንዱ ላይ ካልተጣበቀ በስተቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ እናንተም በእኔ ካልሆናችሁ በስተቀር ፍሬ ማፍራት አትችሉም። እኔ የወይኑ ግንድ ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ እጅግ ፍሬ ያፈራል! ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም።” ዮሐ 15፡ 4-5:: MYPAmh 242.6

እውነተኛውን አምላክ የሚያመልኩ እያንዳንዱን ጣዖት መሰዋት አለባቸው። ኢየሱስ ለጠበቃው “እግዚአብሔር አምላክህን በፍፁም ልብህ፣ በፍፁም ነፍስህና በፍፁም ሀሳብህ ውደደው። ይህ የመጀመሪያው ትዕዛዝ ነው” ብሎት ነበር (ዮሐ 22፡37-38):: ከአሥርቱ ትዕዛዛት የመጀመሪያዎቹ አራት ትዕዛዛት ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር መተዉ እንደሌለበት ይነግሩናል። በእርሱ ያለንን ከሁሉ የበለጠ ደስታ ምንም ነገር ሊጋራው አይገባም። ከእግዚአብሔር ሊለየን የሚችለውን ነገር ሁሉ ካላስወገድን በስተቀር በክርስቲያናዊ ልምምድ ወደ ፊት መቀጠል አንችልም። MYPAmh 243.1

ህዝቡን ከዓለም የመረጣቸው የቤተክርስቲያን ዋና ራስ የሆነው ጌታ እነርሱ ከዓለም እንዲለዩ ይፈልግባቸዋል። የትዕዛዛቱ መንፈስ ተከታዮቹን ወደ ራሱ በመሳብ ከዓለማዊ ነገሮች እንዲለያቸው አቅዷል። እግዚአብሔርን መውደድና ትእዛዛቱን መጠበቅ የዓለምን ደስታና ወዳጅነት ከመውደድ እጅግ የራቀ ነው። በክርስቶስና በሰይጣን መካከል መስማማት የለም። MYPAmh 243.2