መልዕክት ለወጣቶች

419/511

የማይመች ዘመን

ለወጣቶች በማይመች ዘመን ውስጥ እየኖርን ነን። በህብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው ተፅእኖ የተፈጥሮ አእምሮአቸው ወደ መራቸው እንዲከተሉ የሚፈቅድ ነው። ልጆቻቸው መጥፎ ባሕርይ ሲያሳዩ ይህንን ባሕርያቸውን ሲያድጉና በራሳቸው ማገናዘብ ሲጀምሩ ይተውትና ጠቃሚ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ይሆናሉ በማለት ወላጆች ራሳቸውን ያታልላሉ። ይህ እንዴት ያለ ስህተት ነው! ለእነርሱ የደስታ መንገድ የሚመስለው መንገድ የተደበቀ አደጋና አስፈሪ ፍፃሜ ያለው መሆኑን ያልተገነዘቡ በመምሰል የዘመናት ጠላት በልብ የአትክልት ቦታ ዘሩን እንዲዘራ፤ ክፉ መርሆዎች እንዲያድጉና እንዲጠነክሩ ዝም ይላሉ። ብዙ ጊዜ ለእነዚህ ወጣቶች ዘግይተው የሚደረጉ ጥረቶች ምንም አይጠቅሙም። MYPAmh 241.3

ክርስቲያኖች ነን በሚሉት መካከል በአጠቃላይ የብፅእና መስፈርት ዝቅተኛ ስለሆነ ወጣቶቹ በብዙ የቤተክርስቲያን አባላት እየተደፋፈረ ያለውን የዓለም ተፅዕኖ ለመቋቋም ይከብዳቸዋል። አብዛኞቹ የስም ክርስቲያኖች ለክርስቶስ እየኖርን ነን እያሉ በርግጥ እየኖሩ ያሉት ለዓለም ነው። የሰማያዊ ነገሮችን ብልጫ ለይተው ስለማያውቁ በእርግጠኝነት ሊወዱአቸው አይችሉም:: ብዙዎች ክርስቲያኖች ነን ብለው የሚናገሩት ክርስትና የከበረ ነገር ተደርጎ ስለሚታይ ነው። እውነተኛው ክርስትና ማለት መስቀል መሸከም መሆኑን ስለማይረዱ ኃይማኖታቸው ከዓለማዊ ደስታ እንዳይካፈሉ ለማገድ ያለው ተፅእኖ እጅግ አነስተኛ ነው። MYPAmh 241.4

አንዳንዶች ወደ ግብዣ አዳራሽ በመግባት እዚያ ካሉት መደሰቻዎች ጋር አንድነት ይፈጥራሉ። ሌሎች የዚህን ያህል ርቀው ባይሄዱም የደስታ ግብዣዎችን፣ ሽርሽሮችን፣ ፊልሞችንና ሌሎች ቦታዎችን ወይም ዓለማዊ መደሰቻዎችን መከታተል ይችላሉ። ነገሮችን ለይቶ የማየት ችሎታ ያለው ዓይን በእነርሱና በማያምኑ መካከል ያለውን ልዩነት ለማየት ያዳግተዋል። MYPAmh 241.5

በአሁኑ የህብረተሰብ ሁኔታ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመቆጣጠርና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን የትክክለኛነት ህግ ማስተማር ቀላል ነገር አይደለም። ልጆች ብዙ ጊዜ ቁጥጥር ሲደረግባቸው ትዕግስት የለሾች ይሆኑና የራሳቸውን መንገድ በመከተል ደስ እንዳላቸው መግባትና መውጣት ይፈልጋሉ። በተለይም ከአሥር እስከ አሥራ ስምንት እድሜ ክልል ያሉ ወጣት ጓደኞቻቸው ወደሚሰበሰቡባቸው ዓለማዊ ስብሰባዎች መሄድ ምንም ዓይነት ጉዳት አያስከትልም ወደ ማለት ያዘነብባሉ። ነገር ግን ልምድ ያላቸው ክርስቲያን ወላጆች አደጋውን ማየት ይችላሉ። ልጆቻቸውን የሚገጥሟቸውን የተለያዩ ፈተናዎችና እነዚህ ነገሮች በአእምሮአቸው ላይ የሚኖራቸውን ተፅእኖ ያውቃሉ። ልጆቻቸው እንዲድኑላቸው ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ከእነዚህ ስሜትን ከሚቀሰቅሱ መደሰቻዎች መጠበቅ አለባቸው። MYPAmh 241.6

ልጆች የዓለምን ደስታዎች ለመተውና የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ለራሳቸው ሲወስኑ ጥንቁቅና ታማኝ ከሆኑ ወላጆች ልብ ምንኛ ሸክም ይቀልላቸው ይሆን! በዚህን ጊዜም ቢሆን የወላጆች ሥራ መቆም የለበትም። እነዚህ ወጣቶች ከኃጢአትና ከተፈጥሮ ልብ ክፋቶች ጋር እውነተኛ ጦርነትን ገና መጀመራቸው ስለሆነ የወላጆቻቸውን ምክርና ጥንቃቄ በተለየ ሁኔታ ይሻሉ። MYPAmh 242.1