መልዕክት ለወጣቶች

409/511

የቁንጅና ፍቅር

ታላቁ አምላካችን እንኳን ቁንጅናን አፍቃሪ ነው። የዚህን የማያሳስት ማረጋገጫ በእጆቹ ሥራ ውስጥ ሰጥቶናል። ለመጀመሪያው ወላጆቻችን በኤደን ያማረ የአትክልት ቦታ አዘጋጀላቸው። የተለያዩ አይነት ታላላቅ ዛፎች ለጠቀሜታና ለውበት ከምድር እንዲበቅሉ ተደረጉ:: የተለያየ መልክና ቀለም ኖሮአቸው ልዩ ውበት የተጎናፀፉና አየሩን በሽታቸው የሚያውዱ ያማሩ አበባዎችም ተሰሩ። የተለያየ አይነት ላባ ያላቸው ውብ አእዋፍ ፈጣሪያቸውን ለማመስገን ዝማሬያቸውን ዘመሩ። ሰው እግዚአብሔር ለፈጠራቸው ነገሮች በመጠንቀቅ ደስታን እንዲያገኝና የምግብ ፍላጎቱንም በአትክልቱ ቦታ ከነበሩ የዛፎች ፍሬ እንዲያሟላ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር። MYPAmh 236.6

የመጀመሪያ ወላጆቻችንን የኤደን ቤት እንዲህ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ውብ አድርጎ የሰራው አምላክ ለእኛም የከበሩ ዛፎችን፣ የሚያማምሩ አበባዎችንና በተፈጥሮ ውስጥ ያለውን ውብ ነገር ሁሉ ለደስታችን ሰጥቶናል። የባሕርዩ ትክክለኛ እይታ እንዲኖረን ለማድረግ እነዚህን የፍቅሩ መግለጫዎች ሰጥቶናል። MYPAmh 237.1

በልጆቹ ልብ ውስጥ የቆንጆን ፍቅር ተክሏል። ነገር ግን ይህ ፍቅር በብዙዎች ዘንድ ተዛብቷል። እርሱ የሰጣቸው ጥቅሞችና ውበቶች እየተመለኩ ሰጭ የሆነው ባለ ግርማ አምላክ ተረስቷል። ይህ መጥፎ ምስጋና ቢስነት ነው። በፍጥረት ሥራው ሁሉ እግዚአብሔር ለእኛ ፍቅሩን መግለፁን መቀበልና ልቦቻችንም ለእነዚህ የፍቅር ማረጋገጫዎች ለእርሱ ከሁሉ የበለጠና የተቀደሰ ልባዊ ፍቅር መግለፅ አለባቸው። MYPAmh 237.2