መልዕክት ለወጣቶች
ከእግዚአብN?ር ጋር አጋርነት
በአጠገባችሁ ወሰን የለሽ መልካም አጋጣሚዎች አሉላችሁ፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ እንደ ገለጸው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ «አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆን አናውቅም፡፡ ነገር ግን እርሱ ሲገለጥ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፡፡ ምክንያቱም እርሱን በእርሱነቱ እናየዋለን፡፡ ይህ ተስፋ በውስጡ ያለው •እያንዳንዱ ሰው እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡» በሰዎች ለመከበርና በእግዚአብሔር ለመወደድ ከርካሽና ዝቅተኛ ከሆነ ነገር መመለስና ከፍ ወዳለው ደረጃ መነሳት ለእናንተ የተሰጠ እድል ነው፡፡ MYPAmh 37.1
እግዚአብሔር በየዘመናቱ ላሉ ወጣቶች የሚሰጣቸው ኃይማኖታዊ ሥራ እርሱ ለእነርሱ እንደ ልጆቹ ያለውን አክብሮት ያሳያል፡፡ ራስን የማስተዳደር ስራ ይሰጣቸዋል፡፡ በታላቁ የደህንነትና ሌሎችን ከውድቀት የማንሳት ሥራ ላይ ድርሻ እንዲኖራቸው ይጠራቸዋል፡፡ አባት ልጁን በንግዱ ውስጥ ባለድርሻ እንደሚያደርገው ሁሉ እንዲሁም ጌታ ልጆቹ ከእርሱ ጋር ድርሻ እንዲኖራቸው ይወስዳቸዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሠራተኞች ተደርገናል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡- «እኔን ወደ ዓለም እንደላከኝ እኔም ወደ ዓለም ላክኋቸው፡፡” ስምህ እንደ ክርስቶስ ጠላትና የሰይጣንና የኃጢአት አገልጋይ ተብሎ ከሚጻፍ ይልቅ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንን አትመርጥምን? MYPAmh 37.2
ወጣት ወንዶችና ሴቶች የክርስትና መርሆዎችን በየዕለቱ ሕይወታቸው ለማሳየት የክርስቶስ ፀጋ ሙላት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለክርስቶስ መምጫ የሚደረግ ዝግጅት የተሰጡንን ከፍ ያሉ ጠቃሚ ነገሮቻችንን እንድንለማመድባቸው በክርስቶስ የተሰጠን ዝግጅት ነው፡፡ ባህሪዩን ያማረ አድርጎ ማቅረብ ለያንዳንዱ ወጣት የተሰጠ እድል ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ክርስቶስ አጠገብ የመቅረብ አዎንታዊ ፍላጎት አለ፡፡ እርሱ ብርታታችን፣ ብቃታችንና ኃይላችን ነው፡፡ ለአንዲት ደቂቃም ቢሆን በራሳችን መታመን አንችልም…:: MYPAmh 37.3