መልዕክት ለወጣቶች
ተሃድሶ ያስፈልጋል
በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል የሚነቅፈው ክፋት ቀስ በቀስ ሥር እየሰደደ እናያለን። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ተግባር ምንድነው? አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን አባላት በግልፅ የተቀመጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከመከተል ይልቅ የፋሽንን ትዕዛዝ እየታዘዙ ባሉበት ወቅት የቤተክርስቲያን ተፅእኖ መሆን የሚገባውን ሆኖ መገኘት ይችላልን? እነዚህ ነገሮች በመካከላችን እንዲኖሩ እየፈቀድን እንዴት የመንፈስ ቅዱስን መገኘትና እርዳት እንጠብቃለን? የክርስቶስ ትምህርት ተከታዮች ነን ባሉ ሰዎች ወደ ጎን ተጥሎ እያየን ዝም ማለት እንችላለን? ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ትክክለኛ እይታ ላላቸው ሰዎች እነዚህ ነገሮች ሐዘንና ግራ መጋባትን ያመጣሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳቸው ክርስቲያን እህቶች በድፍረትና በፀሎት ማሰብ የለባቸውምን? በእግዚአብሔር ቃል ለመመራት አይሹምን? ከዓለም ፋሽን ጋር የሚመሳሰል ልብስን ለመሥራት የሚባክነው ትርፍ ሰዓት በቅርበት ልብን ለመመርመርና ቃሉን ለማጥናት መሰጠት አለበት። አለ አስፈላጊ መጋጌጫዎችን ለማዘጋጀት የዋሉና ከመባከን የበለጠ የጠፉ ሰዓታት እውነተኛ መርሆዎችንና ጽኑ ስኬቶችን ለመሻት ባክነው ቢሆን ኖሮ ከወርቅ የበለጠ ጠቃሚ በሆኑ ነበር። የክርስቶስ ተከታዮች ነን እያሉ በተግባር ግን ለባህሪዩና ለፈቃዱ መሃይም የሆኑ ወጣት ሴቶችን ሳይ ልቤን ያመኛል። እነዚህ ወጣቶች ገለባን በመመገብ የረኩ ናቸው። ለእነርሱ የዓለም ብልጭልጭ ከዘላለማዊ ሃብት የበለጠ ዋጋ ያለው ይመስላቸዋል። በማሰላሰልና በትምህርት ማደግ ይችሉ የነበሩ የአእምሮ ኃይሎች ሥራ ፈትተው እንዲተኙ ተደርገዋል። ውጫዊ አለባበስ ከመንፈሳዊ ውበት ወይም ከአእምሮ ብርታት የበለጠ ዋጋ እንዳለው ተደርጎ ስለ ተወሰደ ለአለባበስ ያልተገራ ፍቅር ይንፀባረቃል። MYPAmh 231.1