መልዕክት ለወጣቶች

394/511

በአለባበስ ቁጠባ

ልብሳችን ውድ መሆን የለበትም፡- «ወርቅ ወይም እንቁ ወይም ውድ በሆነ አለባበስ” አይደለም፡፡ ገንዘብ ከእግዚአብሔር የተሰጠን አደራ ነው፡፡ የራሳችንን የኩራትና ታዋቂነት የመፈለግ ፍላጎት ለማርካት እንደፈለግን ልንጠቀምበት የራሳችን ገንዘብ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ልጆች እጅ ያለ ገንዘብ ለተራቡት ምግብ፣ ለተራቆቱት ልብስ፣ ለተጨቆኑት መከላከያ፣ ለታመሙት መታከሚያ ወይም ለድሆች ወንጌል መስበኪያ ነው፡፡ አሁን ለታይታ ወጪ የሚሆነውን ገንዘብ በጥበብ በመጠቀም ለብዙ ልቦች ደስታ ማምጣት ትችላላችሁ፡፡ የክርስቶስን ሕይወት አስቡ፡፡ ባሕርይዩን በማጥናት ራስን የመካድ ሕይወቱን ተካፋዮች ሁኑ፡፡ MYPAmh 227.2

በስመ-ክርስቲያኑ ዓለም ለጌጣጌጦችና ለማያስፈልጉ ውድ ልብሶች የተራቡትን ሁሉ መመገብና የተራቆቱትን ማልበስ የሚችል ገንዘብ እየባከነ ነው፡፡ ድሆችንና ችግር ውስጥ ያሉትን ሊረዳ የሚችልን ገንዘብ ፋሽንና ታይታ እየመጠጠው ነው፡፡ ይህንን የሚያደርጉ ከዓለም የአዳኙን የፍቅር ወንጌል ይቀማሉ…፡፡ MYPAmh 227.3