መልዕክት ለወጣቶች
በቤት ውስጥ በረከት
ጌታ ወጣቶችን «ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ” እያላቸው ነው፡፡ የዓለም አዳኝ ልጆችና ወጣቶች ልባቸውን እንዲሰጡት ይፈልጋል፡፡ ክርስቶስ በብርሐን እንደተመላለሰ በብርሃን በመመላለሳቸው ምክንያት ለእግዚአብሔር ታማኝ የሚሆኑ ብዙ የልጆች ሠራዊት ሊኖር ይችላል፡፡ ጌታ ኢየሱስን ይወዳሉ፣ እርሱን ማስደሰት ደስታቸው ይሆናል፡፡ ስህተታቸው ሲነገራቸው ትዕግሥት የለሾች አይሆኑም፣ ነገር ግን በደግነታቸው፣ በትዕግስታቸው የየዕለቱን የሕይወት ሸክሞች መሸከም እንዲችሉ ወላጆቻቸውን ለመርዳት የሚቻላቸውን ሁሉ በማድረግ የአባታቸውንና የእናታቸውን ልብ ያስደስታሉ፡፡ በልጅነትም ሆነ በወጣትነት እድሜ የጌታችን ታማኝ ደቀ መዛሙርት ሆነው ይገኛሉ፡፡ MYPAmh 216.1
ልጆችና ወጣቶች በልጅነት ዘመናቸው በቤት ውስጥ በረከት መሆን ትችላላችሁ፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወላጆች ያሉአቸውን አመፀኛና የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑና በራሳቸው ፈቃድ የሚመሩ፣ ለወላጆቻቸው የሚያመጣውን አለመመቻቸትም ሆነ ሐዘን ችላ በማለት የራሳቸውን መንገድ ለመከተል የፀኑ ልጆችን ማየት ምንኛ ያሳዝናል፡፡ ሰይጣን የልጆችን ልብ በመግዛት ይደሰታል፣ ከተፈቀደለት በራሱ የጥላቻ መንፈስ ይሞላቸዋል፡፡ MYPAmh 216.2