መልዕክት ለወጣቶች
በቤት ውስጥ ትህትና የጎደለው ንግግር
በቤተሰብ ክበብ ውስጥ ትዕግስት የጎደላቸውን ቃላት በመወርወር የተፈፀመው ጉዳት ምንኛ ከባድ ነው! አንድ ሰው የሚወረውራቸው ትዕግስት የለሽ ቃላት ሌላውም በተመሳሳይ መንፈስና ሁኔታ አፀፋ እንዲመልስ ይመራሉ። ከዚህ ቀጥሎ አፀፋ የመመለስና ራስን ከስህተት ነፃ የማድረግ ቃላቶች ይመጣሉ! እነዚህን በሚመስሉ ቃላት አማካይነት ለአንገቶቻችሁ ካባድና የሚያቆስል ቀንበር ይፈበረካል። እነዚህ መራራ ቃላት በሙሉ ለነፍሳችሁ መጥፎ መከርን ይዘው ይመጣሉ። MYPAmh 212.2
እንደዚህ ዓይነቱን ቋንቋ የሚጠቀሙ ሰዎች ራሳቸውን ለመቆጣጠር ባለመቻል የዚህ ዓይነት ንግግር በመናገራቸው ሀፍረትን፣ ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት ማጣትን፣ በራስ አለመተማመንንና መራር ሐዘንን ይለማመዳሉ። የዚህ አይነት ቃላት ባይነገሩ ኖሮ ምንኛ መልካም ነበር። የፀጋን ዘይት በልብ ውስጥ ማኖር፣ የሚያስቆጡንን ነገሮች ሁሉ ማሰላፍ መቻልና ሁሉንም ነገር ክርስቶስን በመሰለ ገርነትና ትዕግስተ ማሳለፍ ምን ያህል የተሻለ ነበር። MYPAmh 212.3
እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ሁኔታዎች የምታሟሉ ከሆነ ለእናንተም ቃል ኪዳኖቹ ይፈጸሙላችኋል። አእምሮአችሁን በእግዚአብሔር ላይ ካሳረፋችሁ ፈተና ሲመጣባችሁ እጅግ ታላቅ ከሆነው ደስታ ወደ ተስፋ መቁረጥ ወይም ሐዘን ሸለቆ አትወርዱም:: ለሌሎች ጥርጣሬና ጨለምተኝነትን አታወሩም። MYPAmh 212.4
ሰይጣን አስተሳሰባችንን ማንበብ አይችልም፣ ነገር ግን ድርጊቶቻችንን ማየት ይችላል፡፡ ንግግራችንንም ይሰማል! ስለሰብአዊ ቤተሰብ ካለው እረጅም እውቀት የተነሳ የባሕርያችንን ደካማ ጎን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ፈተናዎችን ያዘጋጃል:: ምን ያህል ጊዜ ነው በእኛ ላይ ድል እንዲቀዳጅ በሚያስችለው ምስጢር ውስጥ እንዲገባ የምንፈቅድልት:: እነሆ ቃላቶቻችንንና ድርጊቶቻችንን ተቆጣጥረን ቢሆን ኖሮ እንዴት መልካም ነበር! ቃላቶቻችን የተመዘገቡበት መዝገብ በፍርድ ቀን ሲገለጥ የማናፍርባቸው አይነቶች ቢሆኑ ኖሮ ምን ያህል ጠንካሮች በሆንን ነበር። በእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ቃላቶቻችን አሁን ስንናገራቸው ከሚመስሉን እንዴት የተለዩ ይሆኑ ይሆን። Review and Herald, February 27, 1913. MYPAmh 212.5