መልዕክት ለወጣቶች

363/511

ታማኝነት በቤት ውስጥ ባሉ ኃላፊነቶች

በወጣቶች ላይ እየተሽከረከረ ያለው ከባዱ ሃላፊነት በቤታቸው ውስጥ በፍቅርና እውነተኛ ፍላጎት አባትንና እናትን፣ ወንድሞችንና እህቶችን መባረክ ነው። በቤት ውስጥ ለሌሎች በመጠንቀቅና በመሥራት ራስን መካድንና መርሳትን ያሳያሉ። ይህንን ሥራ በመሥራትዋ አንዲት ሴት በፍፁም አትዋረድም። እሷ ልትይዘው የምትችል የተቀደሰና የከበረ ሥራ ነው:: አንዲት እህት በወንድሞችዋ ላይ ምንኛ ታላቅ ተፅእኖ ልታሳድር ትችል ይሆን! እሷ ትክክለኛ ከሆነች የወንድሞችዋን ባሕርይ ትወስናለች። ፀሎቶችዋ፣ ጭምትነትዋና፣ ፍቅርዋ በቤተሰብ ውስጥ ብዙ ማድረግ ይችላል። MYPAmh 211.1

እህቴ ሆይ፣ እነዚህ የከበሩ እሴቶች መጀመሪያ በአንቺ ውስጥ ከሌሉ በስተቀር ወደ ሌሎች ሊተላለፉ አይችሉም። ያ የአእምሮ እርካታ፣ ፍቅር፣ ጨዋነትና እያንዳንዱን ልብ መድረስ የሚችል የባሕርይ ብሩህነት ልብሽ ለሌሎች የሚሰጠውን በአንቺ ላይ ያንፀባርቃል። ክርስቶስ በልብ ውስጥ ካልነገሠ በስተቀር አለመርካትና የባሕርይ መጣመም ይኖራል። ራስ-ወዳድነት እኛ ለእነርሱ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆንነውን ነገር ከሌሎች ይፈልጋል። MYPAmh 211.2

ነፍስን የሚፈትኑና ድፍረትን የሚጠይቁ ነገሮች ታላቅ ሥራና ታለላቅ ጦርነቶች ብቻ አይደሉም። የየእለቱ ሕይወት የራሱን ግራ መጋባቶች፣ ፈተናዎችና ተስፋ መቁረጦች ያመጣል። ብዙ ጊዜ ትዕግሥትንና ችግርን የመጋፈጥ ድፍረትን ወደ ራሱ የሚስብ ዝቅተኛ ሥራ ነው። ችግሮችን በሙሉ ለመጋጠምና ለማሸነፍ በራስ መተማመንና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። በሁሉም ሥፍራ መጽናኛና ማበረታቻ እንዲሆንልህ ጌታን አብሮህ እንዲቆም አድርገው። Testimonies for the church, volume 3 P. 80-81. MYPAmh 211.3