መልዕክት ለወጣቶች

361/511

ክፍል 11—የቤት ሕይወት

ሰብዓዊነትን ከውድቀት በፊት ወደ ነበረው ሁኔታ መመለስና ከፍ ማድረግ በቤት ውስጥ ይጀምራል። የወላጆች ሥራ የሁሉም ሥራ መሰረት ነው። ህብረተሰብ የተፈጠረው ከቤተሰቦች ስለሆነ የሚሆነውም የቤት አባ ወራዎች/እማ ወራዎች እንደሰሩት ነው። “የህይወት መውጫው” ከልብ ውስጥ ነው። የህብረተሰብ፣ የቤተክርስቲያንና የአገር ልብ ቤተሰብ ነው። የህብረተሰብ ደህንነት፣ የቤተክርስቲያን ስኬትና የአገር ብልፅግና በቤተሰብ ተፅዕኖ ይደገፋል። Ministry of Healing, P. 349. MYPAmh 209.1