መልዕክት ለወጣቶች

354/511

የጠዖት አምልኮ አይነቶች

ይህ ፎቶግራፎችን መሥራትና መለዋወጥ የጣዖት አምልኮ አይነት ነው። ሰይጣን ሰማይን ከእይታችን ለመጋረድ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው። የፎቶ ጣዖቶችን በመሥራት እርሱን አንርዳው። እነዚህ ሰብዓዊ ፊቶች ከሚያመለክቱት ደረጃ ከፍ ወዳለው መድረስ ያስፈልገናል። ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ በፊቴ።” ክርስቶስን እናምናለን የሚሉ የእርሱን ምስል ማንፀባረቅ እንዳለባቸው መገንዘብ አለባቸው። በአእምሮ ፊት መቀመጥ ያለበት ነገር የእርሱ ምስል ነው። የሚነገሩ ቃላት በሰማያዊ መገለጥ የተጫኑ መሆን አለባቸው….። MYPAmh 204.3