መልዕክት ለወጣቶች
አሥራት
ካላችሁ ንብረት ሁሉ ከአስር አንዱ እጅ የእኔ ነው በማለት ጌታ ለይቶታል። ስጦታዎቻችሁ የኔ ስራ ወደ ፊት እንዲቀጥል፣ በጨለማ ለተቀመጡት የእግዚአብሔርን ቃል የሚገልጥ ሕያው ሰባኪ ለመላክ ወደ ግምጃ ቤቴ ይግቡ። ያ ታማኝ ያልሆነው ባሪያ የጌታውን መክሊት ወስዶ በመሬት ውስጥ እንደቀበረው ሁሉ ለእግዚአብሔር የራሱ የሆነውን በመከልከል አደጋ ውስጥ ለመግባት የሚደፍር አለን? እኛም ይህ ሰው እንዳደረገው የራሳችንን ታማኝ አለመሆን ለመሸፈን ጌታን “ጌታ ሆይ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንክበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አወቅሁ! ፈራሁም፣ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርኩት። እነሆም መክሊትህ ይኸውልህ::“በማለት እንኮንን ይሆን? ይህንን ከማድረግ ይልቅ የምስጋና ስጦታዎቻችንን ለእግዚአብሔር አንሰጠውምን? The youth’s Instructor, August 26,1897. MYPAmh 199.2