መልዕክት ለወጣቶች
እግዚአብሔርን ከሐብትህ አክብር
“ያለብኝ የጌታዬ እዳ ምን ያህል ነው?” እያንዳንዱን በረከት ከእግዚአብሔር እጅ እየተቀበልን ለእርሱ ግን ምንም አንመልስለትምን? እርሱም ለራሱ ያስቀረውን አስራት እንኳን አንሰጠውምን? ሁሉንም ነገር ራስን መስዋዕት ከማድረግ እውነተኛ መስመር ወደ ራስን ማስደሰት መንገድ መመለስ ልምድ ሆኗል። ነገር ግን የእርሱን በጎነት ሁል ጊዜ በግድ የለሽነት እየተቀበልን ለፍቅሩ ምንም ምላሽ አንሰጥምን? MYPAmh 198.1
ውድ ወጣቶች ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ሚሲዮናውያን አትሆኑምን? ከዚህ በፊት አድርጋችሁ በማታውቁት ሁኔታ እርሱ እንድትደሰቱበት በነፃ ከሰጣችሁ ነገር በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ ለጌታ ስጦታዎችን የመስጠትን ውድ ትምህርት አትማሩምን? ከተቀበላችሁት ከማንኛውም ነገር የተወሰነው ድርሻ ለሰጪው እንደ ምስጋና ስጦታ ይመለስለት። የተወሰነው ደግሞ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ሚስዮናዊ ስራን ለመስራት ወደ ግምጃ ቤቱ ይጨመር። MYPAmh 198.2